የፕላንና ፕሮግራምና አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት

የፕላንና ፕሮግራም አፈፃፀም  ዳይሬክቶሬት ተግባርናሃላፊነት

የስትራቴጂ ፕሮግራምና ፕሮጀክት ዝግጅቶችን ይመራል ያስተባብራል፤የሴክተሩን የትኩረት መስኮች ከሚመለከታቸው  ዘርፎች ጋር በመሆን እንዲለዩ ያደርጋል፤የሴክተሩ ስትራቴጅዎችና የልማት ዕቅዶች ከሀገር አቀፍ፣ከክልሎች፣ ከአህጉራዊና አለማቀፋዊ የልማት አጀንዳች ጋር ትስስር እንዲኖራቸው ያደርጋል፤የሴክተሩ የኢንቨስትመንት  ማዕቀፍ እንዲያዘጋጅ ያደርጋል፣ውጤታማቱን ይከታተላል፡፡

 

የሚኒስቴሩንየስትራቴጂክዕቅድአፈፃፀምእናየፕሮግራምፖርትፎሊዮበትክክለኛውአያያዝበሚመራል

 • ዋናስትራቴጂካዊአፈፃፀምንያጎለብታል፤
 • ጠንካራየአገልግሎትአቅርቦትእናየደንበኞችተሞክሮአስተዳደርንይመራል፤

የፕላንና ፐሮግራምአፈጻጸምዳይሬክቶሬትተጠሪነቱለፖሊሲ፣ ፕሮግራሞች እና ግንኙነቶች ጄኔራል ዳይሬክተርሆኖየሚከተሉትተግባርናኃላፊነትያከናውናል፡-

 

 • የሚኒስቴሩን ራዕይ እና ግቦች ለማሳካት የሚችሉ ፕሮግራሞችን እና ፕሮጄክቶችን ያዘጋጃል፤
 • ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ፕሮግራሞችን እና ፕሮጀክቶች እንዲሁም ኢንቨስትመንቶች ለይቶ ሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤
 • በሚኒስቴር ደረጃ ያሉ ተነሳሽነቶችን / ፕሮግራሞችን ለመገምገም ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ሞዴሎች ማበጀት የሪስክ ማኔጅመንት መመዘኛዎችን ያዘጋጃል፤
 • በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ራዕይ ላይ የተመሰረተ ኢንቨስትመንት እና ቻርተር ፕሮግራሞችን ይነድፋል፤
 • የፕሮጀክት ሀብቶችን ውጤታማ አጠቃቀም በተመለከተ ለበለይ አካላት ያረጋግጣል፤
 • የፕሮግራም / የፕሮጀክት ግዥ ዕቅድ፣ የጥራት ቁጥጥር፣ የኮንትራት አስተዳደር እና ሪፖርት ስርዓት ይዘረጋል፤
 • በግብርና ሙያ መስክ የአማካሪነትና ሥልጠና አገልግሎት ለመስጠት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ለሚጠይቁ ግልሰቦች ለሚመለከተው የስራ ሂደት በማቅረብና በማስገምገም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል፣የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መረጃ ያደራጃል፣የአገልሎት እድሳት ያድረጋል
 • የሥራ ማስኬጃ ክፍል አፈፃፀም ማሻሻያዎችን እና መለኪያዎች ቅድሚያ በመስጠት ያፀድቃል፤
 • በኘሮግራሞች ሁሉ ላይ የአፈፃፀም ዳሽቦርድን ያዘጋጃል፤
 • ከፍተኛ ተፅእኖ እና ከፍተኛ የመቻል ዕድል ላላቸው የፕሮግራም ሪስክ ማኔጅመንት እቅዶችን ያዘጋጃል፤
 • በኘሮግራም አፈፃፀም ላይ ግልፅነት እንዲኖር ፕሮግራሞች መንደፍ፡፡ አግባብነት ላላቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ግንኙነት ያጠናክራል፤
 • የፕሮግራም አፈፃፀም ስትራቴጂካዊ አካሄድ እንዲኖረው ቀጠይነት ያለው ውጤታማ ስርዓት ይዘረጋል፤
 • የሚኒስቴሩ ግቦችን ለማሳካት የሚኒስቴሩ ሙሉ እይታን የሚያካትት የፕሮግራም ደረጃ ያወጣል፤
 • የበጀት መርሃ-ግብሮች በሰዓቱ መቅረብ መቻላቸውን ያረጋግጠ እንዲሁም ሁሉንም ተግባራዊ እና ቴክኒካዊ ሁኔታዎችን ያሟላ ፕሮግራና ትግበራ ስልት ያደራጃል፤
 • የሥራ ዕቅድ እና ማሻሻያ ፕሮግራሞችን እና እንቅስቃሴዎችን እድገትና ትግበራ ይመራል፤
 • የፕሮግራም ፍላጎትን የሚያሟሉ ውጤታማ የለውጥ አስተዳደር መፍትሄዎችን ይመራል፤
 • ለፕሮጅክት / ፕሮግራም አስተዳደር ሂደቶች የጥራት ቁጥጥር / ማረጋገጫ ስርዓት ይዘረጋል፤

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.