የአፈር ሀብት ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ

የአፈር ሀብት ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለተፈጥሮ ሀብት ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ ሆኖ የሚከተለውን ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡-

 • የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ  የአፈር  ለምነት  ማሻሻያ ቴክኖሎጂዎችን እና አሰራሮችን በማመንጨትና በማላመድ እንዲሁም ተሞክረው ውጤታማ የሆኑ ምርጥ ተሞክሮዎችን በሁሉም አርሶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች እንዲተገበሩ የሚመለከታቸውን አካላት በማስተባበር ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • የአፈርን ለምነት እና ምርታማነት ለማሻሻል የሚያስችሉ የፖሊሲ እና የስትራቴጂ ሃሳቦችን ያመነጫል፣ ሲፀድቁም ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • ከአፈር ለምነት ጋር በተያያዘ ሃገሪቱ የተቀበለቻቸውን አለም አቀፍ ስምምነቶች ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • በሁሉም ክልሎች የአፈር ለምነት ኤክስንቴሽን አገልግሎት ለማስፋፋት የክልሎቹን የመፈፀም አቅም ይገነባል፣ የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፣ የተሟላ ክትትልና ድጋፍ በማድረግም ቴክኖሎጂዎቹ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
 • የአርሶ አደሩን እና የከፊል አርብቶ አደሩን እንዲሁም የግል ባለሃብቱን ግንዛቤ ለማዳበር የአፈር ለምነት ማሻሻያ ቴክኖሎጂዎች ስርፀት ለማፋጠን የሚያስችሉ የአፈር ለምነት ማሻሻያ ትምህርቶችን በመገናኛ ብዙሃን፣ በበራሪ ፅሁፎች ፣በመፅሄቶች እና በፖስተሮች እና በሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች የማስተዋወቅ እና የማስፋፋት ስራ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ይሰራል፤
 • በሃገር አቀፍ ደረጃ በአፈር ለምነት ዙሪያ የሚሰሩ አካላት ተቀናጅተው እንዲሰሩ የሚያስችል የአሰራር ስርአት ይፈጥራል፣ የማስተባበር እና የመቆጣጠር ስራዎችንም ያከናውናል፤
 • የሃገሪቱን የአፈር ሀብት እና ለምነት ደረጃ በማወቅ፣ በመተንተን እና በአፈር ምርመራ ውጤት ላይ በመመስረት እንዲሁም የምርምር ውጤቶችን መሰረት በማድረግ የአፈር ለምነትን የሚያበለፅጉ ቴክኖሎጂዎችን ምክረ ሃሳብ በማዘጋጀት ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
 • ከአፈር ለምነት ስራ ጋር በተያያዘ ለዳይሬክቶሬቱ የሚያስፈልጉ የቢሮ እና የመስክ መገልገያ ቁሳቁሶችንና ግብአቶችን የማሟላት እና የማደረጀት ስራ ይሰራል፤
 • የአፈር ማበልጸጊያ ግብዓቶችን ማምረትና ማሰራጨት ሥራዎች ላይ የተሰማሩ አምራች ድርጅቶችን የግብዓት ጥራት ደረጃ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል እንደ አስፈላጊነቱም የመፈጸም አቅማቸውን ይገነባል፤
 • ለአርሶ አደሩ የሚቀርቡ የአፈር ማበልጸጊያ ቴክኖሎጂዎች የጥራት ደረጃ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ይከታተላል፤
 • ከአፈር ለምነት ማሻሻያ ጋር በተያያዘ በተለያዩ አካላት የሚወጡ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መረጃ በመቀበልና በማደራጀት ለብሄራዊ አጽዳቂ ኮሚቴ ያቀርባል፤
 • ከሀገር ውስጥና ከውጪ በተለያዩ አካላት ለሚገቡ አዳዲስ የአፈር ለምነት ማሻሻያ ቴክኖሎጂዎች ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ይሠራል፡፡

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.