የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ

የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለግብርና ሚኒስቴር ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-

  • የዘርፉን ሥራዎች በማቀድ በማስተባበርና በመምራት፣ የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት፣ በዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራትን በመገምገም በመቆጣጠር፣ በማረጋገጥ፣ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን እና የክትትልና ድጋፍ ሥራዎችን በመምራትና በማስተባበር  የሥራ አመራር ዘርፍን ውጤታማ ያደርጋል ፡፡
  • የሥራ የተቋሙን እስተራቴጂ እቅድ፣ዘርፉንና አመታዊ ዕቅድ፣ማስፈፀሚያ በጀት እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ይገመግማል ትክክለኛነቱን ያረጋግጣል ያፀድቃል፣ ሲጸድቅም ለሚመለከታቸው አካላት ያከፋፍላል፣ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፣ በበላይነት ይመራል፣ያስተባብራል፡፡
  • ለዘርፉ የሚያስፈልጉ በጀት፣የሰው ሀብት እና ግብዓቶቸ እንዲሟሉ ያደርጋል፣አፈፃፀሙን እና ለታለመላቸው አላማ መዋላቸውን ይገመግማል፣ ይከታተላል፡፡
  • በስራ ዘርፉ ስር የሚገኙ ሥራ አስፈጻሚዎችን የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል፣ውጤት ይሞላል ፣ በሥራ አስፈጻሚዎች የተሞሉ ውጤቶችን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ያፀድቃል፡፡
  • የዘርፉን አሰራር ለማዘመን የሚያስችሉ ስልቶችን ይነድፋል አሰራሮችን ያሻሽላል በስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡
  • የሥራ እሰፈፃሚዎችን እና የባለሙያዎችን አፈጻጸማቸውን ይገመግማል፣ይመዝናል፣ ያፀድቃል ፣የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን እንዲበረታቱ ያደርጋል ፣የአቅም ክፍተት ያለባቸውን ባለሙያዎች አቅማቸው የሚጎለብትበትን ስልት ይነድፋል፡፡
  • የሚከናወኑ ስራዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ወጪና ጥራት መሰረት መከናወናቸውን ይገመግማል፡፡
  • የዘርፉን ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡፡

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.