የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈጻሚ

የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት አለው፡-

 • የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ የፖሊሲ ሃሳቦች፣ የህግ ማዕቀፎች፣ የሥራ መመሪያዎች፣ ማንዋሎች፣ የአሠራር ሥርዓቶች ፣ በጥናት ተደግፈው እንዲወጡና እንዲሻሻሉ ይሠራል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፣ ውጤታማነታቸውን ይከታተላል፤
 • የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስራዎችን ውጤታማ የሚያደርጉ ስትራቴጂዎችን ተግባር ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤
 • የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አሰራር በተመለከተ የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር ምርጥ ተሞክሮዎችን እንዲቀሙሩና እንዲስፋፉ ያደርጋል።
 • በአርብቶ አደር አካባቢ የመሬት መጠቀም መብት ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችሉ ጥናቶች እንዲካሄዱ ያደርጋል፤ የጥናት ውጤቱም ወደ ተግባር የሚለወጥበትን መንገድ ያመቻቻል፡፡
 • የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አሰራርን እና የመሬት አጠቃቀም ፖሊሲና ፕላን ዝግጅቱንና አተገባበሩን የሚያግዝ ለባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላትና ለማህበረሰቡ  የግንዛቤ  ማስጨበጫ ስልጠና እንዲከናወኑ ያደርጋል፤ የማስፈፀሚያ አቅምን በማደራጀት ተገቢ የማብቃት  ሥራ እንዲከናወን ያደርጋል፤
 • የመሬት አጠቃቀም ማስተር ፕላን ዝግጅት የሚመራበትን የረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ ፍኖተ-ካርታ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤
 • በአገር አቀፍ ደረጃ እያንዳንዱ ማሳ መሬት ለምን ዓላማ መዋል እንዳለበት እንዲጠና በማድረግ ቴክኒካል ሪፖርት ያቀርባል፤
 • የአገሪቱን የእርሻ፣ የደን፣ የግጦሽ፣ የዉሃ አካላት፣ መሠረተ ልማቶች፣ የኢንደስትሪ ፓርክ የዉሃ አዘል፣ ሜጋ ፕሮጀክቶች እና ለሌሎች የግንባታ ቦታ ሥርጭትና ጠቀሜታ እንዲጠና በማድረግ፤ ለመሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅት ግብዓት እንዲሆኑ ያደርጋል፤
 • የአገሪቱን የመሬት እምቅ ሀብት ደረጃ እንዲጠና በማድረግ የመሬት እንስሳትን የመሸከም አቅም ትንበያ ሥራ እንዲከናወን ያደርጋል፤
 • ከክልል እስከ ቀበሌ የመሬት አጠቃቀም ሥርዓት ግንባታ እንዲዘረጋ እና የመሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅት፣ ትግበራና ቁጥጥር ሥራዎችን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤ ከክልሎች ጋር  ይሠራል፣ ሙያዊ እገዛ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
 • በአገሪቱ በተለያዩ የመሬት አጠቃቀም መካከል ግጭትና ሽሚያ ሲፈጠር በጥናት የተደገፈ የውሳኔ ሃሳብ በማዘጋጀት ለውሳኔ ሰጭ አካላት ያቀርባል፤
 • በአገሪቱ ጎጂ የመሬት አጠቃቀም ላይ የቁጥጥር ተግባር ስለሚከናወንበት ሁኔታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ስትራቴጂ ይቀይሳል፣ ቁጥጥር እንዲደረግም ያደርጋል፤
 • ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላትና የተለያዩ ተቋማትን በመቀናጀት የአገሪቱን ስነ-ምህዳር ቀጠናዎች ክፍፍል እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤
 • ለየአካባቢው ተስማሚ የሆኑ አዳዲስ የጥናትና የምርምር ውጤቶችን ያካተተ የመሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅት ፓኬጆችን እንዲዘጋጁና እንዲተገበሩ ያደርጋል፤ ወቅታዊ የመሬት  አጠቃቀምና ሽፋን ካርታና ሰነድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.