የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች አካትቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዩች አካትቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-

 • የሥራ ክፍሉን ሥራ በመምራት እና በማስተባበር፡፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና የአሠራር ማሻሻያ ጥናቶችን ተግባራዊ መሆናቸውን በማረጋገጥ፣ ለሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሀብት የሚገኝበትን ስልት በመቀየስ፣ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግላቸው በማስተባበር፣ የሴቶችንና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥና መብትና ደህንነትን ያስጠብቃል፡፡
 • የሥራ ክፍሉን እቅድና በጀት ያዘጋጃል፣ ያስተባብራል፣  ይመራል፣  ይተገብራል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ የአፈጻጸም ሪፖርት ለሚመለከተው ያቀርባል፡፡
 • የሥራ ክፍሉን ባለሙያዎች የአቅም ክፍተት በመለየት አቅማቸው የሚገነባበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡
 • የሥራ ክፍሉ ባለሙያዎች የሚያከናውኑትን ተግባራ ይከታተላል፣ የሥራ አፈፃፀም ውጤታቸውን ይገመግማል፡፡
 • ለሥራ ክፍሉ የሚያስፈልጉ ግብአቶች እንዲሟሉ ያደርጋል፣ ለታለመለት ዓለማ በአግባቡ መዋሉን ይከታተላል፡፡
 • የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የወጡ ፖሊሲዎች፣መመርያዎችና ደንቦች እንዲዘጋጁ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ግንዘቤ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
 • የሚዘጋጁ ደንቦች፣  መመሪያዎች፣  ፕሮግራሞችና  እቅዶች  ትግበራ  ላይ  የኤች  አይ  ቪ/ኤድስ፣ አካል ጉዳተኞችን አረጋውያንና አካባቢ ጥበቃ ጉዳይ መካተቱን ያረጋግጣል፡፡
 • የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች የሚመለከቱ ፖሊሲ፣ አዋጅ፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና የተዘረጉ የአሠራር ስልቶች በአግባቡ እንዲተገበሩ ያደርጋል፣መተግበራቸውንም ያረጋግጣል፣ ይገመገማል፡፡
 • የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች እንቅስቃሴን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ የአሠራር ስልቶችን ይቀይሳል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
 • በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች የሚደረጉ የጥናት የምርምር ውጤቶች በመመርኮዝ ሥራው ውጤታማና ቀልጣፋ የሚሆንባቸውን ስልቶች ይቀይሳል፣ ተግባራዊ የሚሆንበትን ስርዓት ይዘረጋል፣ አፈጻጸሙን ያረጋግጣል፡፡
 • ፖሊሲዎችን እና መመሪያዎችን ለመከለስ በጥናት ላይ የተመሠረቱ የመነሻ ሀሳቦችን ያመነጫል፡፡
 • የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚንቀሳቀሱ አጋር አካላት ጋር በዘላቂነት በትብብር ለመሥራት መድረኮችን ያዘጋጃል፣ መግባቢያ ሰነዶችን ይፈራረማል፣ ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፣ አፈፃፀሙን ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያደርጋል፡፡
 • በሚካሄዱ አለም አቀፋዊም ሆነ ሀገራዊ አውደ ጥናቶች፣ ሴሚናሮች፣ ሲምፖዚሞች ላይ በመሳተፍ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
 • የዘርፉ አቻ መሥሪያ ቤቶች ጋር የትብብር ፎረም ያዘጋጃል፣ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በመቀመር ያስፋፋል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
 • የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የገቢ ማስገኛ ስልት ይቀይሳል፣ ሃብት ያፈላልጋል፡፡
 • የተገኘውን ፈንድ አገልግሎት ላይ የሚውልበትን መንገድ ይቀይሳል፣ ይከታተላል፣ አፈፃፀሙን ይገመግማል፡፡
 • የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ፕሮጀክቶችን እና ፕሮፖዛሎች እንዲዘጋጁ ያስተባብራል፣ ለበላይ አካል እና ለለጋሽ ድርጅቶች በማቅረብ ያስገመግማል፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ በማዋል ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፡፡
 • የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍ እንዲደረግ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ድጋፍ ያደርጋል፣ ወቅታዊ ግብረ መልስ እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.