የሰብል ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ

የሰብል ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት አለው፡-

 • በአርሶ አደሩ፣ አርብቶ አደሩና ከፊል አርብቶ አደሩ ችግር ላይ የተመሠረተ የሀገሪቱን የሰብል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚረዱ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅድና የሥራ ኘሮግራም ያዘጋጃል፡፡
 • ለሰብል ልማት አስፈላጊ የሆኑ የአገሮሜት፣ የዘር፣ የማዳበሪያና የማሳ ውስጥ አሰራሮችን ቀጣይነት ያለው ጥቅም የሚሰጡበትን የአሠራርና ስልት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይነድፋል፡፡
 • የሰብል ልማት አሰራሮችን፣ ቴክኖሎጂዎችንና ስልቶችን ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ያሰባስባል፣ ያጠናቅራል፣ ለየሥነ-ምህዳሩ እና ለተጠቃሚው በሚስማማ ደረጃ የሚያሰራጭበትን ስልት ይነድፋል፡፡
 • አዳዲስ የምርምር ግኝቶችን በመለየት በመምራትና በመጠቀም፤ የልማት ፓኬጆችን እና ፕሮግራሞችን እንዲሁም ችግር ፈቺ መፍትሄዎችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ተደራሽ ማድረግ፤ የተሻሻሉ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን በሰርቶ ማሳያዎች በመሞከር፤ በማላመድና በማስፋት ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ ይሰራል፤
 • ከሰብል ልማት ስራዎች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸውን ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ ደረጃዎችና ተግባራትን በባለቤትነት በመምራት ያዘጋጃል/ያሻሽላል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • ከሰብል ልማት ስራዎች ጋር ግንኙነት ያላቸውን የአፈር፣ የብዝሀ ሕይወት፣ የየአከባቢ ጥበቃ፣ የጥበቅ እርሻና የኦረጋኒክ እርሻ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በትብብር ያዘጋጃል፤
 • ከምርምር ማዕከላት የተለቀቁ አዳዲስና የተሻሻሉ የሰብል ልማት ቴክኖሎጂዎችን ይለያል ይመርጣል፣ ሠርቶ ማሳያ ያካሂዳል፣ የፓኬጅ አካል በማድረግ ስልጠና ይሰጣል፣ ለተግባራዊነቱንም ይደግፋል፤
 • የመነሻ ዘር ብዜትን ያስተባብራል፣ ለዘር አባዦች ተደራሽ ያደርጋል፣ ስርዓቶችን  ያዘጋጃል ተግባራዊ ያደርጋል፡ እንዲሁም የዘር ብዜት ሥራን የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፤
 • የአየር ትንበያን መሠረት ያደረገ የሰብል አመራረት ምክረ- ሀሳቦችን ያዘጋጃል፣ ለጠቃሚዎች በተለያዩ የስርጭት ስርዓቶች ተደራሽ ያድረጋል፤
 • የሰብል ልማት ስታትስቲካዊ መረጃዎችን የሚሰበሰቡበት ስልቶች፣ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን ያፈላልጋል፣ ተግባራዊ በማድረግ በአግባቡ ይሰበስባል፣ ያደራጃል፣ ያሰራጫል፤
 • የሰብል ምርት ብክነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን ያቀርባል፣ በሌሎች አካላት የሚተገበሩ ተግባራትን አጠቃላይ ስራውን ያስተባብራል፣
 • ሰብል ልማት ሀገራዊ መረጃዎችን እና ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ ያደራጃል ይይዛል፤
 • የሰብል ልማት ቴክኖሎጂዎችንና ችግር ፈቺ መፍትሄዎችን በኤክስቴንሽን ስርዓቱ እንዲደርሱ ያቅዳል፤ ይተገብራል፤
 • የሰብል ምርትን ለማሳደግ የምርምር ውጤቶችን መሰረት በማድረግ ሙያዊ ምክርና  የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤ ይገመግማል፤ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ይተገብራል፤
 • የአደጋ ችግር በሰብል ልማት በማካተት የአደጋ ስጋት ስፍራዎን ይለያል፣ የቅድሚያ ትንበያ፣ መከላከልና የዝግጁነት እና የድጋፍ ሥራዎችን ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን ይነድፋል፣

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.