የእፀዋት ዘርና ምርት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት

የእፀዋት ዘርና ምርት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት

 


የዕፅዋትኳራንቲን፣ዘርናሌሎችግብዓቶችናምርትጥራትቁጥጥርዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለእርሻልማትዘርፍሆኖየሚከተሉት ተግባራትና ኃላፊነት አለው፡-

 • የዕፅዋት ዘሮችና ምርቶች ሌሎች የዕፅዋት ግብኣቶች /ማዳበሪያና ፀረተባይ/ ወደ ሀገር ውስጥና ውጪ ሀገር ጥቅም ላይ ለማዋል በሚተላለፉት ላይ የጤና፣ የጥራትና ደህንነት የደረጃ ፍተሻ በማድረግ ጉዳት የሚያደርሱ ተባዮች (አረም፣ በሽታና ነፍሰ ተባይ) ከዕፅዋት ዘርና ምርት ጋራ እንዳይገቡ መከላከልና ግብአቱም የአገሪቱን ስታንዳርድ ያሟላ መሆኑ ማረጋገጥ፣
 • በአገር ውስጥ የሚፈልቁና ከአገር ውጭ የሚመጡትን ዝርያዎች ለአርሶ አደሩና ለግል ባለሀብቱ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የጤና፣ የምርትና ሌሎች መስፈርቶች ከነባር ዝርያ ያላቸው አብላጫ ፍተሻ በማድረግ የማጸደቅና የመመዝገብ፣ የቴክኖሎጂው አመንጪ የመብት ጥያቄ ሲያቀርብ በሕጉ መሰረት መብቱ እንዲጠበቅለት የማድረግ፣ የሚባዘው ዘር ስታንዳርዱን ያሟላ መሆኑ በማረጋገጥ ጥራቱ የጠበቀ ዘር ለተጠቃሚው እንዲቀርብ ማድረግና ተወዳዳሪ ጥራት ያለው ዘር ወደ ውጭ ለሚልኩ እልግሎት መስጠት፣
 • የዕፅዋት ምርትና ግብአቶች ጤና፣ ጥራትን ደህንነትን ማረጋገጥ የቁጥጥር አቅም ማሳደግን እና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የሚረዱ የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድና የሥራ ኘሮግራም ያዘጋጃል፡፡
 • ለዕፅዋት ኳራንቲን፣ ዘርና ሌሎች ግብዓቶችና ምርት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ለማረጋገጥ የሚረዱ የፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ፕሪግራሞች ይነድፋል፣ የተለያዩ ሕግ ማዕቀፎች እንዲጸድቁ ማቅረብና ሲጸድቁ ለተግባራዊነታቸው ይሰራል፣ ይከታተላል፡፡
 • ለዕፅዋት ኳራንታይን፣ ለፀረ ተባይና የአፈር ማዳበሪዎች ምዝገባና ቁጥጥር፣ ላልተዘጋጁ የዕፅዋት ምርቶች የምግብ ደህንነት ማረጋገጥ፣ ለዝርያ ለቀቃ፣ ለዝርያ ጥበቃ መብትና ዘር ጥራት ቁጥጥር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸውን ፖሊሲዎች፤ ስትራቴጂዎች፣ ደረጃዎችና ተግባራትን በባለቤትነት በመምራት ያዘጋጃል/ያሻሽላል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
 • ለዕፅዋት ኳራንታይን፣ ለፀረ ተባይና የአፈር ማዳበሪዎች ምዝገባና ቁጥጥር፣ ላልተዘጋጁ የዕፅዋት ምርቶች የምግብ ደህንነት ማረጋገጥ፣ ለዝርያ ለቀቃ፣ ለዕፅዋት ጥበቃ መብትና ዘር ጥራት ቁጥጥር የሚረዱ የህግ ማዕቀፎችን እንዲወጡ ያዘጋጃል፣ እንዲፀድቁ ይከታተላል፣ ሲፀድቁ ያስተገብራል፣
 • የፀረ-ተባይ ምዝገባና አስተዳደር፣ ፀረ-ተባይ ማስወገድን፣ የፋይቶ ሰኒተሪ አገልግሎት አሰራርና ደረጃን፤ የዲዩኤስና ብሄራዊ የዝርያ ሙከራና የዘር ጥራት ቁጥጥር ለማሻሻልና ለማጠናከር የሚረዱ ፕሮጀክቶችን ይቀርጻል፣ ሥራ ላይ እንድውል ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
 • ከሚመለከተው ጋር በመሆን የሀገር ውስጥ ዕፅዋት ኳራንቲን (Domestic Quarantine) ሥርዓት እንዲተገበርና የዘር ጥራት ቁጥጥር ላቦራቶሪዎች በየክልሉ እንዲጠናከሩ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣ አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች ላይ የኳራንቲን ቁጥጥር ጣቢያዎችና የዘር ላቦራቶሪዎች እንዲከፈቱ ሙያዊ እገዛ ያደርጋል፣ ብሄራዊ የዕፅዋት ኳራንቲንና የዘር ጥራት ቁጥጥር ሥርዓት ጋር በቅንጅት የሚሰራበትን መንገድ ያመቻቻል ያስተባብራል፤
 • በመደበኛ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ስምምነቶች፣ የፋይቶሰኒተሪ፣ የምግብ ደህንነት፣ ማዳበሪያ፣ ፀረተባይና ዘር ስብሰባዎችና ኮንፈረንሶች ላይ በመገኘት ለአህጉራዊ የፋይቶሰኒተሪ፣ የምግብ ደህንነት፣ ማዳበሪያ፣ ፀረተባይና ዘር ደረጃ አወጣጥ፣ ያለበት ደረጃ እና መሻሻል ያሉባቸው ጉዳዮች ላይ አስፈላጊዉን ሀገራዊ ግብአት ይሰጣል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፣
 • ለዓለም አቀፍ ንግድ ድርጅት አባልነት መስፈርት ለሆነው ለሰኒተሪና ፋይቶ ሰኒተሪ (SPS) ስምምነት ተግባራዊነት ህጋዊ ማዕቀፎች እንዲዘጋጁና እንዲሻሻሉ ከሚመለከተው ጋር በመሆን ያስተባብራል፤ ይመራል፣
 • ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የተፈቀዱ ዕፅዋት፣ የዕፅዋት ውጤቶችና ሌሎች ቁጥጥር የሚደረግባቸው ቁሳቁሶች (Regulated Articles) እና የግብርና ግብዓቶች እንቅስቃሴ መቆጣጠር እንዲቻል በመረጃ ክምችት ስርዓት (Stock Management System) እና በፀረ-ተባይ ምዝገባ አስተዳደር ስርዓት (Pesticide Registration Management System) ተመዝግቦ እንዲያዝ ያደርጋል፤ ያስተባብራል፣
 • ከሀገሪቱ ተከታታይ የተባይ አሰሳና ቅኝት እንዲሁም በመስኩ ከሚደረጉት ምርምር ውጤቶች መረጃ በመነሳት፣ የኳራቲን ተባዮች ዝርዝር መረጃ ያደራጃል፣ ያሻሽላል፣ ስለ አዳዲስ የተባይ ክስተቶች ለዓለም አቀፍ ዕፅዋት ጥበቃ ኮንቬንሽን መረጃዎችን ያስተላልፋል፤
 • ወደ ውጭ ሀገር የተላከው የሰብል ምርት ተቀባይ ሀገር የምርቱን ጥራት ደረጃና የኳራንቲን ተባይ ክስተት ለመኖሩ ለሚቀርብ ቅሬታ (non-complaints) አስፈላጊዉ የማጣራት ሥራ ተሰርቶ እርምጃ መወሰዱን ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፤ ተመሳሳይ ሁኔታ እንዳይከሰት ክትትል ያደርጋል፤
 • ወደ ሀገር ውስጥ የገባ የዕፅዋት ግብአትና ምርት፣ ውጤቶችና ማሸጊያዎች አስፈላጊ መስፈርቶችን ሟሟላታቸውን ያረጋግጣል ጉድለት ያለበቸውን እንዲስተካከሉ ይደግፋል፣ እርምጃ ይወስዳል፣ በዓለም አቀፍ የቁጥጥር ስምምነትት መሠረት ለላኪው ሀገር ያሳውቃል፣ ይከታተላል፣
 • በሀገሪቱ የመግቢያና መውጫ በሮች አዳዲስ የኳራንቲን መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች እንዲከፈቱ ሀሰብ ያቀርባል፣ ያደራጃል፣ ይከታተላል፤
 • ፀረተባይና ማዳበሪያ በሕጉ መሰረት ተመዝግበው ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ የፀረተባይና ማዳበሪያ ምዝገባና ቁጥጥር አዋጅ እና ደንብ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር የተዛመዱና የሀገሪቱን ጥቅም የሚያስጠብቁና አለም አቀፍ ሰምምነቶችን የተከተሉ መሆናቸውን ይገመግማል፣ እንዲሻሻል ያደርጋል አፈጻጸሙን ይከታተላል ፤
 • ፀረ ተባይና ማዳበሪያ ከተመረተበት ጊዜ ጀምሮ ጥቅም ላይ የዋለውንና ያልዋለውን በዓይነትና በመጠን፣ ጊዜ ያለፈበት የክምችት መጠን እንዲለይ እና በዳታ ቤዝ እንዲደራጅ ያደርጋል፣ በህጉ መሰረትና በአግባቡ አእስኪወገድ በስርዓቱ እንዲያዝ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፣ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመሆን እንዲወገድ ድርሻውን ይወጣል፤
 • በዕፅዋት ምርትና ውጤቶችና ግብአቶች ንግድ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች በሀገሪቱ የንግድ አዋጅ፣ ደንብ የሥራ ብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል፣ በመስፈርቶች መሰረት አሟልተው ለመሥራታቸው ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
 • ጥራቱ የተጠበቀ ከፍተኛ ምርት ለማምረትና ለሰው፣ ለእንስሰትና ለተፈጥሮ አካባቢ ጎጂነታቸው ዝቅተኛ የሆኑ ፀረተባዮች፣ ዘርና ማዳበሪያ ለተጠቃሚው እንዲቀርብ ይቆጣጠራል፣ ይገመግማል፣
 • ላልተዘጋጀ የሰብል ምርት ለሰው ምግብነት ከመዋሉ በፊት ደህንነቱን የሚረጋገጥበት ሁኔታዎች ያመቻቻል፣ ለግባራዊነቱ ይከታተላል፣ ይገመግማል፣
 • የጥራትና ደህንነት መለኪያ ደረጃዎች እንዲዘጋጅላቸው የሚያስፈልጉ ምርቶችን ይለያል፤ ውሳኔ ለተሰጠባቸው ሰብሎች ከሚመለከታቸው ጋር በመተባበር በደረጃ ዝግጅቱ ይሳተፋል፤ በወጣው ደረጃ መሰረት ቁጥጥር እንዲካሄድ ይከታተላል፣ ደረጃ ያላሟሉትን እንደ አግባቡ እንደገና እንዲዘጋጁ፣ እንዲበጠሩ፣ እንዲታከሙና ደረጃውን እንዲያሟሉ ወይም ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ክትትል ያደርጋል፤
 • የሰብል ምርት ጥራትና ደህንነትን የሚመለከቱ አጠቃላይ ሀገራዊ መረጃዎች እንዲሰበሰብና በመረጃ ቋት እንዲቀመጥ፣ እንዲደራጅ፤ ተተንትኖ ጥቅም ላይ እንዲውል ያመቻቻል፣ ለተግባራዊነቱ ይከታተላል፣
 • የሰብል ምርት ጥራትና ደህንነትን በተመለከተ ልምድ ለመቅሰምና የተሻሻሉ አሰራሮችን ለመዘርጋት የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መሠረት ደረገ የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገር ልምዶችን እንዲቀመርና ምርጥ ተሞክሮዎችን በማሰባሰብና በማጠናቀር ስራ ላይ እንዲውሉ ስልጠናዎችን እንዲሰጡ ያደርጋል፣
 • በአገር አቀፍ ደረጃ ከዝርያ ማፍለቅ እስከ ግብይት ባለው የእሴት ሰንሰለት  ትኩረት የሚሹ የዘር ጥርት ቁጥጥር ችግሮችን የመለየትና ቅደም ተከተል (Problem identification and prioritization) በማሲያዝ  ችግሮችን መፍታት በሚያስችል መልኩ ስራውን ይመራል፣
 • ጥራቱን የጠበቀ ዘር ለአርሶ አደሩና ለከፊል አርብቶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ ጠንካራ የቁጥጥር ስርአት መዘርጋት፣
 • የብሔራዊ ወይም ክልላዊ የዝርያ ብቃት ሙከራ እና የዲ.ዩ.ኤስ ሙከራ የሚካሄድበት ቦታ በየስነምህዳሩ እንዲኖር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይሰራል፣ ለስራውም የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶች፣ ግብአቶችና  ባለሙያዎች እንዲሟሉ  ያደረጋል፣ ሙከራዎቹ በአግባቡ እንዲሰሩ ያስተባብራል፣ መሰራታቸውን ይከታተላል ይገመግማል፣
 • የሚቀርቡ አዲስ ዝርያዎችን የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎችን መቋቋም የሚችሉና የህብረተሰቡን የምግብና ስርዓተ ምግብ ዋስትና ከማረጋገጥና የገቢ ምንጭ ከማሳደግ አንፃር የተሻሉ መሆናቸውና ለምዝገባ በሚቀርቡበት ወቅት በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ በግልጽ በሚታዩ ባህርያት ከዚህ በፊት ከሚታወቁ ሌሎች ዝርያዎች የተለየ ስለመሆኑ በተለምዶ የሚታወቅ፣ ዘሩ የሚራባበትን የተለዩ ባህርያትን በሚመለከት በበቂ ሁኔታ ወጥነት ያለው እና ከተደጋጋሚ ማራባትና ማባዛት ዑደት በኋላ የተለየ ባህርያቱን ሳይለውጥ ይዞ የሚቆይ /DUS/ መሆኑን በማረጋገጥ እንዲመዘገቡ ያደርጋል፤
 • የዕፅዋት ዝርያው ሲለቀቅ ይዞት የነበረውን ባህሪያት ጠብቆ መቆየቱን በየጊዜው በሚካሄደው የኢንስፔክሽን ሥራና ከሚቀርቡት ሪፖርቶች በመነሳት ይገመግማል ክፍተቶችን በመለየትና ለችግሩ የሚሆን የመፍትሄ ሀሳብ እንዲቀርብ ያስተባባራል ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤
 • በቴክኖሎጂው ማፍለቅ የሚሰማሩ ለማበረታትna የቴክኖሎጂ አቅርቦትን ለማፋጠን አወዛጋቢ የዝርያ ባለቤትነት ችግርን ለመፍታት የሚያስችሉ ዘመናዊ የአሠራር ዘዴዎችን በማስገባት ጥያቄ ሲቀርብ የዝርያ ባለቤትነትን መብት እንዲሰጥ ያደርጋል፣ አግለግሎቱ በተሟላ መንገድ እንዲሰጥ ሁኔታዎች ያመቻቻል፣
 • የእጽዋት አዳቃዮች መብትን ያስተዳድራል፣ ባለመብቶች በተሰጣቸው መብት መሰረት እየሰሩ መሆኑን ይቆጣጠራል፣ በማይሰሩት ላይ በአዋጁ መሰረት አሰተዳዳራዊ እርምጃ እንዲወሰድ የደርጋል፤
 • ማንኛውም የሚመረትና ተመርቶ ከውጭ የመጣ የዕፅዋት ዘር በዝርያ መዝገብ ላይ መመዝገቡን እና በወጣው መስፈርት መሰረት በመስክና በላቦራቶሪ የጥራት ቁጥጥር ስራዎችን አሟልቶ ማረጋገጫ እንዲሰጠው ያደርጋል፣ ይከታተላል፣ በዘር ኣምራች ድርጅቶች ማሳ ላይ ከተባዛው ዘር ሊገኝ የሚችል ምርት ትመና በማካሄድ ለለተመረተው ዘር መጠን የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ይሰጣል፣ ሙያዊ ድጋፍና ክትትል ይሰጣል፣ ለሥራ አፈጻጸሙም ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣
 • በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ጥረቱን የጠበቀ ምርት ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች አባል (ISTA, UPOV, OECD) እንድንሆንና የዘር ላቦራቶሪዎች እውቅና (Accrediated) እንዲያገኙ በትጋት ይሰራል፤
 • የድህረ ዘር ጥራት ቁጥጥር ሙከራ የሚካሄድበትን ጣቢያ የሚለይበትን፣ ሙከራው ተግባራዊ የሚደረግበትን የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፣ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤ የሙከራውን ውጤት ይገመግመል፣ የሙከራ ውጤቱ ለበላይ አካልና ለተጠቃሚው ሪፖርት እንዲቀርብ ያደርጋል፡፡
 • የዘር ብዜት ማሳዎችን ትክክለኛ መጠናችውን ለማወቅ በጂፒኤስ የመለካትና GIS ቴክኖሎጂ ካርታ መሰራታቸውን ይከታተላል፣ በዘር ኢንዱስትሪው ለተሰማሩ አካላት የውስጥ ጥራት ቁጥጥር ኣቅማቸው ለማሳደግ ስልጠና እንዲሰጥ ያደርጋል፣ የተሰጠውንም ስልጠና በተግባር ላይ መዋሉን ይገመግማል፣ በዘር እሴት ሰንሰለት ድርሻ ካላቸው አካላት ጋር የቀረበ ግንኙነት በማድረግ በሥራ ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ይለያል፣ የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀምጣል፣
 • በዳይሬክቶሬቱ የምርምር ሥራ የሚሹ ችግሮችን በመለየት ምርምር እንዲካሄድባቸው ሀሳብ ያቀርባል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ ውጤቱንም ከሌሎች ጋር በመሆን ይገመገማል፣ ግብረ-መልስም ይሰጣል፣
 • በዳይሬክቶሬቱ ስር ለሚገኙ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች፣ በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሀብቶች የአቅም ግንባታ፣ ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና የሚያገኙበት ስትራቴጂ ይቀይሳል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣ የምክር አገልግሎት ይሰጣል፤ ይገመግማል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣

የዕፅዋት ኳራንቲን፣ ዘርና ሌሎች ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አጠቃላይ ሥራዎችን ዕቅድ ያዘጋጃል፣ አፈፃፀማቸው ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ መረጃዎችን ያደራጃል፣ ወቅታዊ የዕፅዋት ኳራንቲን፣ ዘርና ሌሎች ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ያለበትን ሁኔታ ሪፖርት ያደርጋል፡፡

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.