ግብርና ሜካናይዜሽን አቅርቦት ዳይሬክቶሬት

ግብርና ሜካናይዜሽን አቅርቦት ዳይሬክቶሬት

የግብርና ሜካናይዜሽን ግብዐት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ተግባርና ሃላፊነት

ይህ ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለግብርና ግብዓትና ምርት ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፤

  • ተገቢ የግብርና ሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት ምንጮችን የግዢ ስልት፣ እቅድ ፣ፖሊሲ፣ አሰራርና ፣ መመረያዎችን መፈተሽና ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፤
  • የግብርና ሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት ከጠቅላላው የግብአት አቅርቦት ስልት አንጻርመቅረጽ ይመራል፤
  • ግዢ፣ ማከማቸትና ማሰራጨት የስራ እንቅስቃሴዎች የጥራትና ብቃት ፣ የዋጋ ተወዳዳሪነት እንዲሁም የላቀ አገልግሎት ለውስጥና ለውጭ ተገልጋዮች ከመስጠት አንጻር ያለውን እንቅስቃሴ በመፈተሽ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
  • የስራ ዕቅድ ማዘጋጀት ተግባራዊ ያደርጋል፤
  • ተፋሰስ ልማት በሚካሄድበት አከባቢ የሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት ሥራዎች ያሉበትን ደረጃና ችግሮችን ለመፍታት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት መነሻ የሚሁኑ መረጃዎችን ማሰባሰብ፣ መለየት፤
  • የተሰበሰቡ የሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት መረጃዎችን የማደራጀት፣ ለዘመናዊ መረጃ ቋትና ፣ለዕቅድ ዝግጀት ያመቻቻል፤
  • የሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት  ሥራ በአከባቢው ያለበትን ደረጃና የህበረተሰቡን ልማዳዊ አሠራር በመለየት የተሰበሰቡ መረጃዎጨችን መሰረት በማድረግ ቀላል ትንታኔ መስጠት፣ በአግባቡ ያደራጃል፤
  • በአከባቢው የሚተገበሩ የተፋሰስ ልማትና ከሌሎች የግብርና ልማት ሥራዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ የሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት ለማስፋፋት የሚያስችሉ አዳዲስ ውጤቶችና የተሸሻሉ አሰራሮች በማሰብሰብ ለቴክኒክ አሰራር ዝግጅት ግብዓት ያደርጋል፤
  • የሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት በተመለከተ ለሚዘጋጁ የአጭር ጊዜ ፕሮጀክቶች፣ አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን፣ ህጎች ፣ ደንቦችና መመሪያዎች መረጃዎችን ያሰባስባል፤
  • የግብርና ሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት  በሚመለከት በተዘጋጀው የስልጠና ሰነድ መሰረት ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና መስጠት የሚሰጥበትንም ሁኔታ ያመቻቻል፤
  • በተፋሰስ ልማት የሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት ሥራዎች ለማስፋፋት የተቀመሩ አዳዲሰና የተሸሻሉ ቴክኖሎጂዎችና መመሪያዎችን ማሰራጨት ፣ ተግባራዊነታቸውን በመከታተል ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፤
  • በተፋሰስ ልማት ተግባራዊ የሚደረጉ የሜካናይዜሽን  ግብአት አቅርቦት ሥራዎች በተዘጋጀው ዕቅድና መመሪያ መሰረት እንዲከናውኑ ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት ይከታተላል፤
  • የተፋሰስ ልማት ሥራዎች በሚታቀደበትና ተግባራዊ በሚደረጉበት ሥራዎች ውስጥ የሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት በተዘጋጀው የአሰራር ማኑዋል መሠረት እንዲተገበሩ ድጋፍ ማድረግ፣ መከናወናቸውንም ውጤታማነታቸውን መከታተል ሪፖርት ያደርጋል፣

Please publish modules in offcanvas position.

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.