የከተማ እና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት ድጋፍ ዳይሬክቶሬት
የከተማናኮሜርሺያልግብርና ድጋፍ ዳይሬክቶሬቱተግባርናኃላፊነት
የከተማና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨስትመንት በዓለም የኤክስፖርት ገበያ ተመራጭና ተወዳዳሪ የሆነ የከተማ እና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት ምርት እንዲሁም ለሀገር ውስጥ ለምግብ ዋስትናና ኢንዱስትሪዎች ግብዓት በብቃትና በጥራት ለማቅረብ እንዲቻል የግብርና ኢንቨስትመንት የአቅም ግንባታና የድጋፍ አገልግሎት ሥራዎችን በማስተባበር አማራጮችን በማስፋት ከዘርፉ የሚገኘውን ሀገራዊ ጠቀሜታ ማሳደግ ይሆናል፡፡
የከተማ እና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት ድጋፊ ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለግብርና ኤክስቴንሽን፣ ማስፋፊያ እና የአቅም ግንባታ ጀነራል ዳይሬክቶሪት ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና እና ሀላፊነት ይኖሩታል፡፡
- የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል፣ የተዘጋጀውን ዕቅድ ለዳይሬክተር ጄነራሉ እና ለሚመለከታቸው ኃላፊዎች እንዲሁም ለክልሎች ያቀርባል፣ ሀሳቦችን ያሰባስባል፣ በእቅዱም ውስጥ ያካትታል፣ ያፀድቃል፣ሲጸድቅም የበጀት ጥያቄ ለሚመለከተው አካል እንዲቀርብ ያደርጋል፣ ሲፈቀድ ተግባራዊ ያደርጋል፣
- የዳይሬክቶሬቱን ስራዎች በፀደቀው ዕቅድ መሠረት ለሥራ ቡድኖችና ለባለሙያዎች በማከፋፍል ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣
- የከተማ እና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት ፈጣን ዕድገትና ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ የፖሊሲ ሀሳቦች፣ ስትራተጂዎችና ማስፈጸሚያ ስልቶችን ያዘጋጃል፣ ለሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ያቀርባል፣ የስፀድቃል፣ ሲፈቀድ ተግባራዊ ያደርጋል፣ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፣
- ከክልሎች ጋር በመተባበር ለከተማ እና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት በጥናት የተለዩ መሬቶችን መረጃዎችን በማሰባሰብ ያደራጃል፣ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ያደርጋል፣
- ከክልሎች፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና ከውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጋር በመተባበር በክልሎች ለከተማ እና ለኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት የተዘጋጀውን መሬት የተስማሚነት (የሰብል፣ የሆርቲካልቸር፣ የመኖ ልማት፣ የራንች …ወዘተ) ደረጃ ሰነድ ከዳይሬክተር ጄነራሉ ጋር በመሆን በተለያዩ ዘዴዎች ለባለሀብት ያስተዋውቃል፣ አስፈላጊውን መስፈርት ላሟሉ ባለሃብቶች ከክልሎች መሬት እንዲያገኙ ያመቻቻል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
- የከተማ እና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት የአቅም ግንባታ ስትራቴጂ በማዘጋጀት ይተገብራል፣ የክህሎት ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል ስልጠና በአጫጭርና መካከለኛ ሥልጠናዎች ለባለሙያዎች እና ለአምራቹ አቅም ግንባታ ድጋፍ እንዲያገኙ ያመቻቻል፣
- የከተማ እና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች በአውትግሮወርስና ኮንትራት እርሻ አሰራር የአካባቢው አርሶ/አርብቶ አደሮች ጋር እንዲተሳሰሩ የተቀናጀ ድጋፍ ይሰጣል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
- ለከተማ እና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት የሚያስፈልጉ የመሰረተ ልማት እና ሌሎች ግብአቶች አቅርቦት በወቅቱና በተፈለገው መጠንና ጥራት እንዲቀርብ ከሚመለከታቸው ጋር በመተባበር ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ የሚሰጡ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች(የባንክ ብድር፣ ከቀረጥ ነፃ የገቡ የእርሻና ተጓዳኝ መሳሪያዎች…ወዘተ) ለተፈቀደላቸዉ አላማ መዋላቸውን ይከታተላል፣
- ከክልሎች ጋር በመቀናጀት የከተማ እና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት መሬቶች አጠቃቀምና ቢዝነስ ፕላን አተገባበር በተገባው ውል መሠረት ስለመሆኑ ክትትልና የሙያ ምክርና ድጋፍ ይሰጣል፣ አስፈላጊ ሲሆን የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ያስደርጋል፣ የብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል፣
- ከክልሎች ጋር በመተባበር በከተማ ግብር እና ኮመርሻል እርሻዎች ኢንቨስትመንት የወጣቶችን ተሳትፎ በማሳደግ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ድርሻን ለማሳደግ እንዲቻል የወጣቶችን ፍላጎትና ሊሰማሩ የሚችሉባቸውን የሥራ መስኮች በጥናት መለየትና ወደ ከተማና ግብርና ኢንቨስትመንት የሚገቡበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
- የከተማ እና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት የምርት ማሰባሰብ አሰራር በማጥናትና የሌሎች አገሮች ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር እና አስፈላጊውን ድጋፍ በማመቻቸት አገልግሎቱን እንዲሻሻል ያደርጋል፣የተቀመረውን ተደራሽ ያደርጋል፣
- ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመሆን የከተማ እና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት ምርቶች በተለይም የኤክስፖርት ምርቶች በዋጋና በጥራት ተወዳዳሪነታቸዉን ለማረጋገጥ በተሻለ አመራረት፣ ምርት እንክብካቤ፣ ጥራትና መጠን እንዲመረት ያደርጋል፣ የባለሀብት ኤክስቴንሽን ፓኬጆችና ማኑዋሎች ከሚመለከታቸው ዳይሬክቶሬቶች ጋር እንዲዘጋጅ በማድረግ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግ የአዋጭ አማራጭና ውጤታማ ፓኬጆች እንዲዘጋጁ በማድረግ ለአገልግሎት ተጠቃሚዎች እንዲደርስ ያደርጋል፣
- የከተማ እና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት ማነቆዎች እና መልካም አጋጣሚዎችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ጥናት ያጠናል፣ ይተነትናል የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል፣
- በክትትልና ድጋፍ ዳሰሳ ጥናት ወቅት የተደረጉትን ጥናቶች መሰረት በማድረግ በአመራረት እና በምርት ጥራት እና በሌሎች ልማት ስራዎች የሚታዩ ክፍተቶች ከምርምር ተቋማት የሚገኙ የምርምር ስራዎችን በማካተት ፓኬጅና ማኑዋል እንዲዲዘጋጅ ያደረጋል፣ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣
- ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚረዱ ጥናቶች እንዲካሄዱ በማድረግ፣ አቅም ግንባታ ስልጠና እንዲሰጡ በማመቻችት፣ ክትትል፣ ድጋፍና የምክር አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ፣ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችንና አሰራሮችን እንዲለዩ በማድረግ ለተጠቃሚው እንዲደርስ ያደርጋል፡፡
- የከተማ እና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ቋሚ የምክክር መድረክ/ፎረም በማዘጋጀት በጋራ ለልማቱ እድገት የሚያግዙ የውሳኔ ሀሳቦች በመውሰድ ተግባራዊ ያደርጋል፣
- ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት የከተማ እና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት የተመለከቱ የሀገር ውስጥና የውጭ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ያስፋፋል፤ አምራቾች በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ንግድ ትርዒቶች እንዲሳተፉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ በዘርፉ እሴት ሰንሰለት የሚታዩ ማነቆዎችን ለመፍታት የሚያስችሉ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ የጥናት ዉጤቶች ሥራ ላይ የሚዉሉበትን ስልቶችና አሠራሮችን ያዘጋጃል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
- በከተማ እና የኮመርሻል ግብርና ኢንቨስትመንት ወደ ልማት የገቡ መሬቶች፣ የምርት እንዲሁም ተያያዥ መረጃዎችን ያሰባስባል፣ የማደራጀት፣ የመተንተንና ለተጠቃሚዎች ተየመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን ተከታትሎ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣ የህግ ውሳኔዎች ተፈፃሚነት ይከታተላል፣ የአካባቢው ህብረተሰብ እሴቶችና ባህሎች ተጠብቀው እንዲፈፀም ያደርጋል፣
- ከከተማ እና ኮመርሻል ግብርና ኢንቨትመንት ልማት አንጻር የዳይሬክተር ጄነራሉና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ወክሎ ግንኙነቶችን ያደርጋል፤
- የዳይሬክቶሬቱ ተገልጋይ እርካታ ማረጋገጫ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣ በቢሮና በመስክ የተሰጡ አገልግሎች እርካታ ማሰበሰቢያ ቼክሊስት ያዘጋጃል፣ እርካታውን ይለካል፣ ግብረ መለስ ይሰጣል፣
- በተጨማሪም ከዳይሬክቶሬት ጄነራሉ የሚሰጡ ሥራዎች ያከናውናል፣