የአበባ ልማት ዳይሬክቶሬት
የአበባልማትዳይሬክቶሬትተግባርናሃላፊነት
የአበባ ልማት ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡
- ተገልጋዮች የሚፈልጓቸውን የአገልግሎት አይነቶች በአግባቡ መለየት፣ ወቅታዊ በማድረግ ተደራሽነታቸውን ማረጋገጥ፤
- በወሳኝ የአበባ እርሻ ሥራ ወቅቶች በመስክ በመገኘት ሙያዊ ድጋፍና የምክር አገልግሎት መስጠት፤
- ወቅታዊ የሜቲዮሮሎጂ እና የበሽታና ተባይ ክስተት መረጃዎች ያሰባስባል፣ ያደራጃል ለተጠቃሚዎች ያቀርባል፣ ምክር አገልግሎት መስጠት፤
- በአበባ ልማት እርሻዎች የተሰማሩ ባለሀብቶች አፈጻጸም ለማሳደግና ምርታማነትንና ጥራትንና ለመጨመር የሚረዳ የኤክስቴንሽን ስርዓት መዘርጋት፣ ተግባራዊነቱን መከታተል፤
- የአበባ አምራች ባለሀብቶችን አቅም በተከታታይ ለማሳደግ የሚረዳ የአቅም ክፍተትና የስልጠና ፍላጎት የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ አስተያየት ማቅረብ፤
- የክፍሉን ፈጻሚዎች አቅም ክፍተት በመለየት ሥልጠና የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤
- ለባለሀብቱና ሌሎች አልሚዎች ልማት አዋጪና ውጤታማ የሆኑ ምርጥ የአበባ ልማት ቴክኖሎጂዎችና ተሞክሮዎችን በማሰባሰብ፣ መተንተን፤ መቀመር፣ የሚስፋፋበትን ሰርዓት መዘርጋት፤
- የተዘጋጁ ቴክኖሎጂዎችና ምርጥ ተሞክሮዎችን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ በማድረግ በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማስፋት እንዲቻል የአሰራር ማንዋል ማዘጋጀት፣ ተግባራዊነቱን መከታተል፤
- ከዩኒቨርሲቲዎች እና ግብርና ምርምር ተቋማት ጋር በቅርበት በጥናትና ምርምር ስራ ተቀናጅቶ መስራት፤
- መካከለኛ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንዲቻል የአበባ ልማት ተግባር ማሰልጠኛ ተቋማትን ማጠናከር፤
- የሚመለከታቸው ዩኒቨርስቲዎች ካሪኩለም የማሻሻል ስትራቴጂና የትምህርት አሰጣጡም ለዘርፉ ውጤታማነት አስተዋፅኦ በሚያደርግ መልኩ እንዲሆን ግንዛቤ እንዲጨብጡ ማድረግ፤
- ለአበባ ልማት ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉትን ነባር የግብርና ማሰልጠኛ ማዕከላት በመለየት፣ ለተቋማት የበጀትና የቁሳቁስ ምንጭ በማፈላለግ ተቋማቱን ማጠናከርና አዳዲስ የግብርና ማሰልጠኛ ማዕከላት ማቋቋም፤
- የአምራቹ፣ የኮንትራት አርሶ አደሩና የአዉትግሮወሩን አቅም በስልጠና በመደገፍ አሰራሩ እንዲጎለብት ማድረግ።
- አዉትግሮወሮች በግሎባል-ጋፕ ሰርቲፋይ እንዲሆኑ በማብቃት መስፈርትን ጠብቆ የመስራት ልምድ እንዲያዳብሩ ማድረግ፤
- በአውትግሮወርስና ኮንትራት እርሻ ስርዓት ከአልሚዎችና ባለሀብቱ ጋር የሚተሳሰሩ የአካባቢው አርሶ አደሮች የላቀ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የኢንተርፕሪነርሽፕ ስልጠና መስጠት፤
- ለዘርፉ ልማት አዋጪና አስፈላጊ የሆኑ ከስልጠናና ቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ መረጃ አደራጀቶ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ፤
- ባለሀብቱና ሌሎች ተገልጋዮች የሚፈልጉትን የድጋፍ ጥያቄዎች የቀረጥ ነጻ፣ የውጭ ዜጋ የሥራ ፈቃድ፣ የፈቃድ እድሳት ወዘተ/ በተቀላጠፈና በተቀናጀ ሁኔታ ጥራት ባለው መልኩ እንዲያገኙ ማድረግ፤
- የአበባ ልማት መሬት የተረከቡ ባለሀብቶች በገቡት ውልና ባቀረቡት የአዋጭነት ጥናት ሰነድ መሰረት ልማት ማከናወናቸውን የአፈጻጸም መከታተያና መገምገሚያ መስፈርትና ደረጃ (Standard) ማዘጋጀት፣ ተደራሽ ማድረግ፤
- የአበባ ልማት የሚካሄድባቸውን አካባቢዎች ለክትትልና ድጋፍ በሚመች መልኩ በወቅት፣ በዝርያ አይነት፣ በተግባራት ዓይነትና በአካባቢ በመለየት የቁጥጥር፣ ክትትልና ድጋፍ ክላስተር ማዘጋጀት፣ መገምገም፤
- በአበባ ልማት እርሻዎች የተሰማሩ ባለሀብቶች የብቃት ማረጋገጫ አሰጣጥ ሥርዓትና ማንዋል ማዘጋጀት፤ ሲፈቀድ ተግባራዊ ማድረግ፤
- በተዘጋጀው ክትትልና ድጋፍ ማዕቀፍ መሰረት በየክላስተሩና በየወቅቱ ክትትል በማድረግ ችግሮችን መለየት፣ የተደራጀ መረጃ መያዝ፣ የድጋፍ ዕቅድ ማዘጋጀት፣ የተዘጋጀውን የድጋፍ ዕቅድ ለሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ማሰራጨት፤ መፈጸማቸውን ክትትል ማድረግ፤
- በተደረገው ክትትል መሰረት በተለዩ ችግሮች ዙሪያ ተወሰዱ እርምጃዎችንና መፍትሄዎችን ችግር ፈቺነትና ተፈጻሚነት ይከታተላል መቆጣጠር፤
- የአበባ ልማት እርሻዎች የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በሚያግዝና በሚያሻሽል መልኩ እንዲከናወንና የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ለማድረግ የሁኔታ ዳሰሳ በማደረግ ለአመራሩና ለአካባቢው ማህበረሰብ ስልጠና እንዲሰጥ ማድረግ፤ ትስስር የሚፈጠርበትን አግባብ መጠቆም፤
- የአበባ ልማት እርሻዎችን ለማበረታታት ለአልሚዎችና ባለሀብቶች የሚሰጡ የተለያዩ ማበረታቻዎች በታሰበው መንገድ ጥቅም ላይ መዋላቸውን ይመዘግባል፣ ይከታተላል፣ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት መስራት፤
- በአበባ ልማት እርሻዎች የሚካሄድባቸው አካባቢዎች በመሰረተ ልማትና አስፈላጊ ግብዓት አቅርቦት የተሟሉ እንዲሆኑና ለባለሀብቱና ሌሎች አልሚዎች አዋጭ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ በትብብር መስራት፤
- ለቀጣይ ክትትልና ድጋፍ የእያንዳንዱ አልሚ እና ባለሀብት ደረጃ የሚያሳይ ፕሮፋይል ማዘጋጀት፤ ለሚመለከተው የበላይ አካል አቅርቦ እንዲገመገም ማድረግ፡፡