ግብርና ሜካናይዜሽን አቅርቦት ዳይሬክቶሬት
ግብርና ሜካናይዜሽን አቅርቦት ዳይሬክቶሬት
የግብርና ሜካናይዜሽን ግብዐት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ተግባርና ሃላፊነት
ይህ ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለግብርና ግብዓትና ምርት ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፤
- ተገቢ የግብርና ሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት ምንጮችን የግዢ ስልት፣ እቅድ ፣ፖሊሲ፣ አሰራርና ፣ መመረያዎችን መፈተሽና ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፤
- የግብርና ሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት ከጠቅላላው የግብአት አቅርቦት ስልት አንጻርመቅረጽ ይመራል፤
- ግዢ፣ ማከማቸትና ማሰራጨት የስራ እንቅስቃሴዎች የጥራትና ብቃት ፣ የዋጋ ተወዳዳሪነት እንዲሁም የላቀ አገልግሎት ለውስጥና ለውጭ ተገልጋዮች ከመስጠት አንጻር ያለውን እንቅስቃሴ በመፈተሽ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
- የስራ ዕቅድ ማዘጋጀት ተግባራዊ ያደርጋል፤
- ተፋሰስ ልማት በሚካሄድበት አከባቢ የሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት ሥራዎች ያሉበትን ደረጃና ችግሮችን ለመፍታት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት መነሻ የሚሁኑ መረጃዎችን ማሰባሰብ፣ መለየት፤
- የተሰበሰቡ የሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት መረጃዎችን የማደራጀት፣ ለዘመናዊ መረጃ ቋትና ፣ለዕቅድ ዝግጀት ያመቻቻል፤
- የሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት ሥራ በአከባቢው ያለበትን ደረጃና የህበረተሰቡን ልማዳዊ አሠራር በመለየት የተሰበሰቡ መረጃዎጨችን መሰረት በማድረግ ቀላል ትንታኔ መስጠት፣ በአግባቡ ያደራጃል፤
- በአከባቢው የሚተገበሩ የተፋሰስ ልማትና ከሌሎች የግብርና ልማት ሥራዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ የሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት ለማስፋፋት የሚያስችሉ አዳዲስ ውጤቶችና የተሸሻሉ አሰራሮች በማሰብሰብ ለቴክኒክ አሰራር ዝግጅት ግብዓት ያደርጋል፤
- የሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት በተመለከተ ለሚዘጋጁ የአጭር ጊዜ ፕሮጀክቶች፣ አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን፣ ህጎች ፣ ደንቦችና መመሪያዎች መረጃዎችን ያሰባስባል፤
- የግብርና ሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት በሚመለከት በተዘጋጀው የስልጠና ሰነድ መሰረት ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና መስጠት የሚሰጥበትንም ሁኔታ ያመቻቻል፤
- በተፋሰስ ልማት የሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት ሥራዎች ለማስፋፋት የተቀመሩ አዳዲሰና የተሸሻሉ ቴክኖሎጂዎችና መመሪያዎችን ማሰራጨት ፣ ተግባራዊነታቸውን በመከታተል ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፤
- በተፋሰስ ልማት ተግባራዊ የሚደረጉ የሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት ሥራዎች በተዘጋጀው ዕቅድና መመሪያ መሰረት እንዲከናውኑ ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት ይከታተላል፤
- የተፋሰስ ልማት ሥራዎች በሚታቀደበትና ተግባራዊ በሚደረጉበት ሥራዎች ውስጥ የሜካናይዜሽን ግብአት አቅርቦት በተዘጋጀው የአሰራር ማኑዋል መሠረት እንዲተገበሩ ድጋፍ ማድረግ፣ መከናወናቸውንም ውጤታማነታቸውን መከታተል ሪፖርት ያደርጋል፣