የገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ ዳይሬክቶሬት
የገጠርስራዕድልፈጠራዳይሬክቶሬትተግባርናሃላፊነት
የገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለተፈጥሮ ኃብትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ሃላፊነት ይኖሩታል፤
- በገጠር አካባቢ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና ዘላቂ ልማት ለማምጣት የሚያስችል የአካባቢውን ዕምቅ ሀብት መሰረት ያደረገ የሴት እና ወንድ ተገልጋዮችን ፍላጎትና ዝንባሌ የሚያሳይ የዳሰሳ ጥናት ያካሄዳል፣
- የገጠር ስራ እድል ፈጠራን ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚያስችል የክትትልና ግምገማ ስርዓትና የትግበራና የአፈጻጸም መመሪያዎች (Manuals and Guideines) በማዘጋጀት ባለድርሻ አካላት እንዲያውቁዋቸውና ሥራ ላይ እንዲያውሏቸው ያደርጋል፤
- በገጠር ስራ ፈላጊ የህብረተሰብ ክፍሎችን ፍላጎትን፣ ዝንባሌንና የአካባቢውን እምቅ ሃብት (potential) መሰረት በማድረግ በማህበር እንዲደራጁ ያነሳሳል፣ ተደራጅተው በሚፈጠረው አማራጭ የስራ ዕድል እንዲሰማሩ ይደግፋል፣
- በተለያዩ የትምህርት ተቋማት በተለያየ ሙያና ትምህርት ተመርቀው ስራ ለሚፈልጉ ወንድና ሴት ወጣቶች ከሙያቸዉና ዝንባሌያቸዉ አንጻር አዋጭ የሆኑ የስራ አማራጮችን በመለየትና በማጥናት በገጠርና ከተማ ግብር እና ሌሎች አማራጭ የስራ መስኮች እንዲፈጠሩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- በገጠር ለሚኖሩ ሥራ ፈላጊ የህብረተሰብ ክፍሎች ከማሳ ዉጪ ግብርና ነክ እና ግብርና ነክ ያልሆኑ አማራጭ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር የአከባቢዉን ልምድና ተጨባጭ ሁኔታ መሠረት ያደረገ ጥናት ያካሄዳል፡፡
- ከሚመለከታቸው የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል፣ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችንም በትብብር ያካሂዳል፡፡
- በገጠር በጥናት በተለዩ የስራ አማራጮች የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ውጤታማ ለማድረግ የመስሪያና የመሸጫ ቦታ፣ የመሰረተ ልማት አቅርቦት፣ የስልጠና፣ የብድርና የገበያ ድጋፎችን እንዲያገኙ ያደርጋል፣
- በገጠር በግብርና ምርቶች ላይ ተጨማሪ እሴት የሚፈጥሩ አማራጭ የስራ እድሎችን ያጠናል፣ አዋጭነቱን በማረጋገጥ ፓኬጅ ቀርፆ ወደ ተግባር እንዲሸጋገር ይደግፋል፡፡
- በገጠሩ አካባቢዎች በተፈጠሩ የስራ አማራጮች የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከምርታቸው ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የገበያ ጥናት ያካሄዳል፤ትስስር ይፈጥራል፤ ገበያ መር ምርቶች ላይ እዲሰማሩ ያበረታታል፣ቀጣይነት እንዲኖረው ክትትል ያደርጋል፡፡
- በገጠር አካባቢዎች የተፈጠሩ የስራ አማራጮች በከተሞች አከባቢ ከተቋቋሙ ወይም ከሚቋቋሙ ኢንተርፕራይዞች ጋር በሚተሳሰሩበት ሁኔታ ላይ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል፡፡
- በጥናት ለተለዩት አማራጭ የስራ ዕድሎች የፋይናንስ ፍላጎትን ቀጣይነት ባለው መልኩ ከማሟላት አኳያ ፈንድ የሚገኝበትን ስልት ይነድፋል፡፡
- በገጠር አማራጭ የስራ ዕድሎችን በመደገፍ ሂደት የሚሳተፉ የተለያዩ ግብረ-ሰናይ እና ሌሎች የልማት ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ይፈጥራል፣
- በገጠር ካለዉ ተጨባጭ ሁኔታና ችግሮች በመነሳት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ያላቸዉን ዘርፎች ያጠናል፣ ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ያደርጋል፣
- የተሻለ ተሞክሮ ካላቸው ተቋማት ጋር የልምድ ልውውጦች እንዲካሄዱ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ በተጨማሪም በየተግባሩ የሚገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር ወደ ሌሎች ያስፋፋል፤ የሌሎች አካባቢዎችን ምርጥ ተሞክሮዎች በመቀመር ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
- በዳይሬክቶሬቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች ማለትም የብድር፣ የመረጃ፣ የንግድ ሥራ አመራር፣ ተስማሚ ቴክኖሎጂና የጥሬ ዕቃ አቅርቦት፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ የሂሳብ መዝገብ አያያዝና የኦዲት አገልግሎቶች እና በስራ ሂደቱ በየደረጃው የሚከናወኑ ሌሎች ተግባራት በተዘጋጀላቸው ስታንዳርድ መሠረት በአግብቡ መሰጠታቸውን ይከታተላል፣አፈፃፀማቸውን ይገመግማል፣ለሠራተኞችም ግብረ-መልስ ይሰጣል፤
- የስራ እድል ፈጠራው የሴቶችን እኩል ተጠቃሚነት ያረጋገጠ እንዲሆን ያደረጋል፡፡
- በስራቸው ውጤታማ ለሆኑ ኢንተርፕራይዞች፤ማህበራት እና ቡድኖች ማበረታቻ ይሰጣል፣
- ለዳይሬክቶሬቱ የሚያስፈልገውን ዕቅድና ሪፖርት ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣