የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ መሪ ሥራ አስፈጻሚ
የተፈጥሮ ሀብት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ተግባርና ኃላፊነቶችም፡-
- በገጠር ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ለማጠናከር የሚያግዙ መመሪያዎችን ማዘጋጀት፣ አዳዲስ የፖሊሲ ሀሣቦችን ማመንጨት፣ ሲፈቀዱም ተግባራዊ ያደርጋል፣
- የተፋሰስን መርህ የተከተለና የተጠቃሚውን ኅብረተሰብ በንቃት ባሳተፈ መልኩ በተለያዩ ተፋሰሶች የባዮፊዚካል፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎች በማሰባሰብና በመተንተን ያሉትን የልማት ችግሮችና አለኝታዎች በመለየት ከኅብረተሰቡ ፍላጎትና ከአየካባቢዎቹ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር የተገናዘበና የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ዕቅድ በማዘጋጀት ተግባራዊ እንዲደረግ ድጋፍ ይሰጣል፣
- በተፋሰስ ልማት፣ በማኅበረሰብ ሥራዎች እና የአፈር ሀብት ልማት ስትራቴጂ ላይ ያተኮረ በየደረጃው የሚገኙ ባለሙያዎችን ዕውቀትና ክህሎት በማሳደግ የመፈፀም ብቃታቸውን ለማጎልበትና በየደረጃው የሚታዩ የአቅም ክፍተቶችን በመለየት የሚስተዋሉ የአቅም ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችሉ የአሰልጣኞች ሥልጠናዎችን መስጠት፣ አገር አቀፍ ዐውደ-ጥናቶችና ሴሚናሮች ማካሄድ፤
- በግብርና ሚኒስቴር በኩል የአየር ንብረት ለውጥን፣ የድርቅ እና የአደጋ ተጋላጭነት ለመቋቋም የሚረዱ ሥራዎችን መከታተል፣ ለተግባራዊነታቸው ድጋፍ መስጠትና ውጤታማነታቸውን በመገምገም የማሻሻያ ሀሣቦችን ማቅረብ፣
- የተፈጥሮ ሀብት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ዙሪያ የሚሰሩ የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በቅንጅት ይሠራል፤