የአነስተኛ መስኖ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ
የአነስተኛ ይዞታ መስኖ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ለተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ተጠሪ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡
- የአነስተኛ መስኖ ልማትንና የአነስተኛ መስኖ አውታሮች አስተዳደርና ውሃ አጠቃቀም ብቃት ለማሳደግና ለማጠናከር ፖሊሲዎችና መመሪያዎችን ማዘጋጀትና ማቅረብ፣ አዳዲስ የፖሊሲ ማሰፈጸሚያ ስትራቴጂዎችን ማመንጨት፣ ሲፈቀዱም ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የማህበራዊ ምጣኔና የዘላቂ አካባቢያዊ ልማትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ የመስኖ ውሃ መገኛ አካላትንና አማራጮችን ማጥናትና መረጃዎችን በተጠናከረ መልኩ ማደራጀት፣ መመርመርና መተንተን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን አፈጻፀማቸውን መከታተልና ሪፖርት ማድረግ፤
- በሃገር አቀፍ ደረጃ እየለማ ያለውን የመስኖ መሬት መጠን የመረጃ ክፍተት ተዓማኒ በሆነ መልኩ በዘለቄታዊነት ያለውን የመሬት መጠንና የውሃ ማልማት አቅም ጅኦ-ሪፈረንስና ሪሞት ሴንሲንግ ተክኖሎጂ በመታገዝ መረጃን በመያዝና በመተንተን በመስኖ በይነ መረብ የመረጃ ስርዓት ውስጥ ማደራጀት፤
- ብቃት ያለው የአነስተኛ መስኖ አውታሮች አስተዳደርና ውሃ አጠቃቀም ሥርዓት ለማስፈን
- የአነስተኛ ይዞታ መስኖ ልማት እንዲስፋፋ የፖሊሲና ስትራቴጂ አቅጣጫዎችን መንደፍ፣ ሲፈቀዱም ከክልሎች ጋር በቅንጅት ተግባራዊ ማድረግና አፈፃፀማቸውን መከታተል፣
- የአነስተኛ ይዞታ መስኖ ልማት አውታሮች ቅድመ ግንባታ (ጥናትና ዲዛይን)፣በግንባታ ወቅትና ድህር ግንባታ የመስኖ ተጠቃሚው ማህበረሰብ ሚና ድርሻና ሃላፊነትን በመለየት፤የመስኖ ልማት ፈንድ ምንጮችን በመለየት መተግበሪያ መመሪያና አሰራር ስርዓት መዘርጋት፤
- ከተቋሙ ራዕይና ተልዕኮ በመነሳት የሥራ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፤
- የሥራ ሂደቶች ቅንጅትና ትስስር በማጥናት የተጠናከረና ተመጋጋቢነት ያለዉ የሥራ ግንኙነት እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
- ከሥራ ዕቅዱ በመነሳት ለዳይሬክቶሬቱ የተመደበዉ በጀት በትክክል ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ይቆጣጠራል፣ ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤