የዕፅዋት ጥበቃ መሪ ሥራ አስፈጻሚ
የዕፅዋት ጥበቃ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለእርሻ ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት አለው፡-
- በአርሶ አደሩ፣ አርብቶ አደሩና ከፊል አርብቶ አደሩ ችግር ላይ የተመሠረተ የሀገሪቱን የሰብል ምርትና ምርታማነትን የሚቀንሱ መደበኛና ተዛማች ተባዮችን ጉዳት ለመቀነስ የሚረዱ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅድና የሥራ ኘሮግራም ያዘጋጃል፤
- ለዕፅዋት ጥበቃ አስፈላጊ የሆኑ አሰራሮችን ቀጣይነት ያለው ጥቅም የሚሰጡበትን የአሠራርና ስልት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይነድፋል፤
- የዕፅዋት ጥበቃ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ላይ የተመሠረተ የተቀናጀ የተባይ መከላከል አሰራሮችን፣ቴክኖሎጂዎችንና ስልቶችን ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ያሰባስባል፣ያጠናቅራል፣ለየሥነ-ምህዳሩ እና ለተጠቃሚው በሚስማማ ደረጃ የሚያሰራጭበትን ስልት ይነድፋል፡፡
- ከዕፅዋት ጥበቃ ሥራዎች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸውን ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ ደረጃዎችና ተግባራትን በባለቤትነት በመምራት ያዘጋጃል/ያሻሽላል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- ለተባይ ምርመራና ልየታ አገልግሎት የሚሰጥ ደረጃውን የጠበቀ ላብራቶሪዎች እንዲኖሩ ሀሳብ ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ እንዲሆን ይመራል፣ ያስፈፅማል፤
- የዕፅዋት ጥበቃ የተባይ ልየታ ዲያግኖስቲክስ፣ ቁጥጥርና መከላከል አገልግሎት ብቃት ለማሻሻል የሚረዱ አሰራሮች፣ አቅጣጫዎችና ቴክኖሎጂዎችን ያፈላልጋል፣ ይለያል፣ ተግባረዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
- በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ያሉ የዕፅዋት ጥበቃ ክሊኒኮችን አቅም በመገንባት የተባይ ቁጥጥር፣ ቅኝትና መከላከል አገልግሎት አሰጣጥ እንዲያድግ ይደግፋል፣ ፕሮጀክቶች ይቀርፃር፣ ተግባራዊነቱን ይመራል፣ ይደግፋል፤
- የድንበር ዘለል ተዛማች ወረሪሽኝና መደበኛ ነፍሳት ተባዮች፣ ዕፅዋት በሽታ፣ መጤ ወራሪና መደበኛ አረሞች የክስተት ስጋት ጥናት፣ ክትትል፣ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ መሠረት ቀድሞ የመከላከል ሥርዓት ዝርጋታ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል፤ ውሳኔው ተቀባይነት ሲያገኝ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- በዘመናዊና ሳይንሳዊ ስልት የሚካሄድ የዕፅዋት ተባዮች፣ የክስተት ክትትል፣ ስጋት ጥናትና ቅኝት፣ መረጃ መሰብሰብ፣ መተንተን፣ ቁጥጥርና መከላከል ሥራ አሰራሮችን ይነድፋል፣ ተሞክዎችን ይለያል፣ ይቀምራል፣ በሀገሪቱ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያስተባብራል፣ ይመራል፤
- ድንበር ዘለል ተዛማች ተባዮች መከሰት ምቹ ሁኔታ መፈጠር አለመፈጠሩን ቀድሞ ከዓለም አቀፍና ሀገራዊ ሜቲዎሮሎጅ መረጃ መሰብሰብ፣ በመተንተን ከዓለም አቀፍ ትንበያ ጋር በማገናዘብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ማዘጋጀትና ቀድሞ ለመከላከል የሚረዳ በጀት፣ የመከላከያ ግብዓቶችን፣ ሎጅስቲክ ቅድመ ዝግጅት ያደርጋል፣
- ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ የተቀናጀ የተባይ መከላከል ቴክኖሎጅ ፓኬጆች ያዘጋጃል፣ በየጊዜው ይከልሳል፣ ስልጠና ይሰጣል፣ ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፤