የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ
በሚኒስቴር ዴኤታ የሚመራ የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ተጠሪነቱ ለግብርና ሚኒስቴር ሆኖ የሚከተለውን ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡-
- የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ምርታማነት ለማሻሻል ለአርሶ አደሩ፣ ለአርብቶ አደሩ፣ ለግል ባለሀብቱና በሰብል ልማት ለተሰማሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጡ የኤክስቴንሽንና የስልጠና አገልግሎት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
- የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ልማትን የሚያፋጥኑና ከየግብርና ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸውን የፖሊሲ፣ የስትራቴጂና ፕሮግራም ሀሳቦችን በማመንጨት እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሲፈቀድም እንዲተገበሩ ደርጋል፣ ይመራል፤
- ሀገራዊ የዕፀዋት ዘረመል ሀብት እንዲለይ፣ እንዲመረጥ፣ እንዲሻሻል፣ ጥቅም ላይ እንዲውልና እንዲጠበቅ ሥርዓት እንዲዘረጋ ከምርምር፣ ከዩንቨርሲቲዎችና ከብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩት ጋር ይሠራል፤
- የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ምርትና ምርታማነት የሚያሻሻሉ የምርምር ሥራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር የሚሰሩበት ሥርዓት ይዘረጋል፣ ሲፀድቅም እንዲተገበር ያደርጋል፣ ይመራል፤
- የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ የአየር ንብረት ለውጥ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ተመጋጋቢነት እንዲጎለብት ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታታላል፣ ይመራል፤
- ስነ-ምህዳርና ከባቢ አየርን መሠረት ያደረጉ የግብርና አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን በሰብል አመራረት ስርዓቱ ውሰጥ ውጤታማነትና ዘላቂ ልማት በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲተገበሩ ያደርጋል፣ በዘርፋ የሚሰሩ አካላትንም ይደግፋል፣
- የመነሻ ዘር ብዜትን ያስተባብራል፣ ስርዓቶችን ያዘጋጃል ተግባራዊ ያደርጋል፣ እንዲሁም የዘር ብዜት ሥራ የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያገኝ ያደርጋል፣
- የአየር ንብረት መረጃን መሠረት ያደረገ የሰብል ልማት ምክረ ሀሳብ በዘመናዊና ተደራሽ በሆነ መልኩ ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ ያደርጋል፤
- የምርት ብክነትን ለመቀነስ እና የምርት ጥራትን ለማሻሻል የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮችን ይለያል፣ የምርምር ስራዎች እንዲሰሩ ይደግፋል፣ ለአርሶ አደሩና ለግል ባለሀብቱ እንዲደርሱ ያደርጋል፣ ውጤታማነታቸውን ይገመግማል፤
- የመደበኛ ተባዮች ጉዳትን ለመቀነስ የሚረዱ ከዘር ጀምሮ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ከባቢ አየርን በማይጎዳ መልኩ ተደራሽ ያደርጋል፤
- የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍን ለማዘመን የሚረዱ ዕውቀትና ክህሎትን ለማሻሻል የሚያግዙ ስልጠናዎች ይለያል፣ የአጭርና የረጅም ጊዜ አቅም ግንባታዎች እንዲሰጡ ያደርጋል፣ የስልጠና ማዕከላት የልህቀት ተቋማት እንዲቋቋሙ ያደርጋል፣ ይመራል፤
- ለእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ምርታማነትና ዕድገት ዘለቄታዊ ልማት አጋዥ የሆኑ ስትራቴጂዎችንና አቅጣጫዎችን በማሳየትና በማዘጋጀት የሀብት ምደባ በማመቻቸት የቁጥጥርና ክትትል ድጋፎችን በማድረግ የግብርናን ይመራል፤
- ለዕቅድና ለውሳኔ አሰጣጥ ድርሻ ያላቸውን የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ መረጃዎች ከባለደርሻ አካላት ጋር በመሆን ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
- የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ግቦችን ሊያሳኩ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን፣ፓኬጆችንና አሰራሮችን ይለያል፣ ይመርጣል፣ ቴክኖሎጂዎችና የመፍትሄ ሀሳቦች በኤክስቴንሽን ስርዓቱ እንዲስፋፉ ይመራል፣ ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፤