የዘርፍ ስትራተጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ
የግብርና ስትርተጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ የሚከተለውን ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡-
- የመሥሪያ ቤቱን የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅዶች እንዲዘጋጁ በማድረግ፡ የተቋሙን በጀት በአግባቡ እንዲዘጋጅ በማድረግ እና በማስተዳደር፡ የተቋሙን የመረጃ አያያዝና አጠቃቀም ስርዓት በማዘመን ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ፡ የመሥሪያ ቤቱን እቅድ አፈጻጸም ላይ ክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ በማድረግ፡ የልማት ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን ክትትል ድጋፍና ግምገማ በማድረግ የተቋሙን ግብ እና ዓላማ ያሳካል፡፡
- የክፍሉን ሥራ እቅድ ያዘጋጃል፣ ለቡድኖች ያከፋፍላል፣ ይገመግማል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፡፡
- የክፍሉን ሥራ ከሌሎች የሥራ ክፍሎች ጋር ያለውን ቅንጅትና ትስስር በማጥናት የተጠናከረና ተመጋጋቢነት ያለው የስራ ግንኙነት እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ አፈጻጸሙንን ይከታተላል ይደግፋል፡፡
- በክፍሉ ስር የሚገኙ ሰራተኞች በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩና ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት እንዲሰጡ ያለባቸውን የአፈጻጸም ክፍተት ይለያል፣ እንዲበቁ ያደርጋል፡፡
- ለክፍሉ የሥልጠና፣ የማቴሪያል ፍላጎቶችና ለሥራ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን እንዲሟላ ያደርጋል፣ያደራጃል፡፡
- የሚዘጋጁት የፕሮጀክት፣ እቅድ ለቡድን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች መድረሱን ይከታተላል፣ የፕሮጀክት ሥራዎችን በበላይነት ይመራል፡፡
- የፖሊሲ ስትራቴጂና የፕሮግራም የፓኬጆችና የፕሮጀክቶች ሀሳቦች ያመነጫል፤ የዶክመንት ዝግጅትና ማሻሻል ሥራውን በመምራት የጸደቀ ዶክመንት ለሚመለከታቸው አካላት እንዲሰራጭ ያደርጋል፡፡
- ለዘርፉ ሥራ የሚያግዙ የህግ ማእቀፎችን፣ የሥራ መመሪያዎችን፣ ማንዋሎችን፣ ስነ- ስርዓቶችን እና መግለጫዎችን በአዲስ መልክ እንዲወጡና እንዲሻሻሉ ያደርጋል፣ የሚዘጋጁትን ሰነዶች ለሚመለከታቸው አካላት እንዲሰራጩ ያደርጋል፡፡
- የሥራ ዘርፉንና የመሥሪያ ቤቱን ዕቅድ ዝግጅት፣ አፈጻጸምና የክትትልና ግምገማ ሥራዎች ሊያሻሽሉና ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ የጥናትና የምርምር ሥራዎች እንዲካሄዱ ሀሳብ ያመነጫል ፤ያስተባብራል፤ የጥናቱን ውጤት ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤ ፋይዳውን በመገምገም ሪፖርት ያቀርባል፡፡
- የተቋሙን የመረጃ አያያዝና አጠቃቀም ስርዓት በማዘመን ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
- የተቋሙን የተለያዩ የስራ ክፍሎችን የልማት አመላካቾችን በማዘጋጀት ውጤትን መሰረት ያደረገ የልኬታ ስርዓት ይቀርፃል፣ ይዘረጋል፡፡
- የመሥሪያ ቤቱን ስትራቴጂክና አመታዊ እቅድ ያዘጋጃል፤ እንዲዘጋጅም ያደርጋል፤ የክትትልና ድጋፍ፣ የግምገማና ግብረ መልስ ሥራዎችን በኃላፊነት ይመራል፣ ያስተባብራል፣ በበላይ ኃላፊው እያፀደቀ ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡
- የእቅድ ዝግጅትና ሪፖርት፣ የግምገማና ግብረ-መልስ ሥራዎች ውጤታማና ቀልጣፋ እንዲሆኑ ያሠራር ስርዓቶችን ይዘረጋል፡፡
- የተቋሙንና የዘርፉን የሥራ እቅድና አፈጻጸም የተሳካ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በሚደረገው ውይይትና አውደ ጥናቶች ላይ በመገኘት አስፈላጊ ግብአት ግብአት ይወስዳል፤ ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡
- የተቋሙን በዓመት ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የመደበኛ፣ የካፒታል፣ የእርዳታና ብድር በጀቶችን እቅድ በማዘጋጀት በመተንትንና በማማከር ለሚመለከተው አካል አቅርቦ ያፀድቃል፡፡
- ለፕሮግራሞችና ለፕሮጀክቶች የተመደበ በጀት ለታለመለት አላማ መዋሉን ይከታተላል፣ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- ለግንባታ የተመደበ በጀት ለታለመለት አላማ መዋሉን ይከታተላል፣ድጋፍ ያደርጋል፣ ርክክብ ይፈፅማል፡፡
- ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮጅክቶችን ወደ ስራ እንዲገቡ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡
- የፀደቀ በጀትን በአይቤክ በአግባቡ መመዝገቡን ይከታተላል፡፡
- የበጀት ዝውውር ጥያቄ ሲቀርብ አግባብነቱን በመመርመር የውሳኔ ሃሳብ ለበላይ ሃላፊው ያቀርባል ሲወሰንም ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
- የበጀት አጠቃቀም ሪፖርት ያዘጋጃል ይገመግማል፣ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ግብረ- መልስ ይሠጣል፡፡
- በቡድኖች የሚቀርቡ የፕሮጀክት አፈጻጸም መረጃዎችን ሰነዶችን ያጠቃልላል፤ በባለሙያዎች የተዘጋጁ የፕሮጅክት ሰነዶችን ትክክለኛነቱን ያረጋግጣል ፡፡
- የተዘጋጁ ረቂቅ የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ይገመግማል፤ ማሻሻያ ያደርጋል፡፡
- የተዘጋጁ የፕሮቶኮል ስምምነቶችን በመ/ቤቱ ሃላፊ እንዲረጋገጥ በማድረግ ለሚመለከታቸው እንዲሰራጩ ያደርጋል፡፡
- የፕሮጀክት ዝግጅትና ክትትል ስራዎችን የሚያቀላጥፉ የአሠራር ሥርዓቶችና ዘዴዎችን ይቀርጻል እና ያሻሽላል፡፡
- የፕሮጀክት ዕቅድ፤ የኮትራት ሥራዎችን የውል ስምምነት ሰነዶችን ያዘጋጃል፡፡
- ፕሮጀክቶች በተያዙለት የጥራት ደረጃ፣ የጊዜና የበጀት መርሃ ግብር መሰረት እየተከናወኑ መሆኑን ይከታተላል፡፡
- ሥራው ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም በተመለከተ እና ለፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚሆን ፈንድ አመንጭ የሚሆኑ ፕሮጀክቶችን ለማግኘት መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ይገናኛል፤ ፈንድ ያፈላልጋል፡፡
- የአገሪቱን የልማት አቅጣጫ ስትራቴጅክ እቅድና የስራ ክፍሎችን የስራ ባህሪይ መሠረት ያደረጉ የፕሮጀክት እቅድ ሰነድ ትክክለኛነት ያረጋግጣል፡፡
- የመስሪያ ቤቱን ሥራ በተመለከተ ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ልማት ድርጅቶች የሥራ ግንኙነት ያደርጋል፣ይከታታላል፡፡
- መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሚያቀርቧቸውን የልማት ፕሮጀክቶች ሰነድ ከመንግስት ፖሊሲና ስትረተጅ ጋር መጣጣሙን ይመዝናል፣ የማስተካከያ ሀሳቦችን ይሰጣል፣ይገመግማል መስሪያ ቤቱን በመወከል ይፈራረማል፡፡
- በፕሮግራሙ የተቀመጠው በጀት ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ከአጋር አካላት ጋር በመሆን የመስክ ምልከታ በማድረግ የማሻሻያ ሀሳብ ያቀርባል፡፡
- የፕሮግራሞችንና የፕሮጀክቶችን የመካከለኛና የማጠቃለያ ዘመን አፈፃፀም ግምገማ ያደርጋል፡፡
- የሚቀረፁ ፕሮጀክቶች የፕሮጀክቱን አዋጭነት ለመወሰን መሟላት ያለባቸው የፕሮጀክቶችን መሠረታዊ ይዘቶች ማለትም የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ አዋጭነት፣ የቴክኒክ አግባብነት እና አካባቢያዊ ተፅዕኖ ግምገማ በአካተተ መልክ መዘጋጀቱን ይከታተላል፣ያረጋግጣል፡፡
- የአጋር አካላት ግንኙት፣ሀብት ማሰባሰብና ፕሮጀክት አስተዳደር ስርዓትን ይዘረጋል፣ እንዲሻሻል ያደርጋል፣አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
- ለዘርፉ ሥራዎች የተለያዩ የፋይናንስ አማራጮች እንዲለዩ ያደርጋል፣ ከተለያዩ የልማት አጋር አካላት ሀብት የማፈላለግ ተግባርን በኃላፊነት ይመራል፣ ያስተባብራል፡፡
- የፋይናንስ ድጋፍ በሚገኝባቸው የፕሮጀክት አማራጮች ላይ ከልማት አጋር አካላት ጋር ድርድር ያካሂዳል፣ያስተባብራል፣አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ያረጋግጣል፡፡
- የዘርፉ መረጃዎቹ በዘመናዊ መልክ እንዲደራጁና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋል፣ መሰጠቱን ያረጋግጣል፡፡
- በተለያዩ ፎርማቶች የተሰበሰቡትን መረጃዎች ውስጣዊ መጣጣም የሚፈተሸበትንና መረጃዎች ላይ የሚታዩ ችግሮች ካሉ ካሉ ኤዲት ስፔስፊኬሽን ሰርቬይ እንዲዘጋጅና ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
- የዘርፉ መረጃዎች በአግባቡ መሰብሰባቸውን፣ መጠናቀራቸውንና መተንተናቸውን በክትትልና ድጋፍ እንዲረጋገጥ ያደርጋል፣ ያረጋግጣል፡፡
- ለመረጃ ትንተና የሚረዱ ሞዴሎችን እንዲመረጡ መደረጉን፣ የተለያዩ ከፍተኛ ውስብስብነት ያላቸው መረጃዎች ሞዴሎችን መሰረት በማድረግ እንዲተነተኑ መደረጉን ያረጋግጣል፡፡
- በዘመናዊ መረጃ ቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ ዳታ ቤዝ እንዲደራጅ ያደርጋል፡፡
- ለባለድርሻ አካላት የሚሰራጩ የተለያዩ ስታቲስቲካዊ እና ሌሎች መረጃዎችን በአይነት እና በጥራት እንዲዘጋጁና እንዲሰራጩ ያደርጋል፡፡
- ዓመታዊ ስታትሰቲክስ መጽሄቶች፣ በራሪ ጽሁፎች፣ ኒውስ ሌተሮች፣ ብሮሹሮች፤ እንዲዘጋጁና እንዲታተሙና እንዲሰራጩ ያደርጋል፡፡
- የተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ ዘዴዎችን በመጠቀም እንዲሠራጩ ያደርጋል፡፡
- መንግስት ከግሉ ዘርፍ ጋር ሊሰራ የሚችልባቸውን መስኮች የአዋጭነት ጥናት ለመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት ቦርድ በማቅረብ እንዲፀድቅ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
- በመንግስትና በግል አጋርነት ሊሰሩ በተመረጡ መስኮች የግል ዘርፉን ለማሳተፍ የጨረታ ሰነድ ዝግጅቱን የጨረታ አወጣጥ ሂደቱን ይመራል፣ ያስተባብራል፡፡
- በመንግስትና በአሸናፊው የግል ዘርፉ በተቀመጠው የትብብር ስምምነት መሰረት ስለመፈፀሙ ይከታተላል፣ያረጋግጣል፡፡
- ለግል ዘርፉ የሚሰጠው አገልግሎት የተሳለጠ (Ease of Doing Business) እንዲሆን ያደርጋል፣ያስተባብራል፡፡
- ለግሉ ዘርፍ ሁሉ አቀፍ የሆነ አገልግሎትን ለማሳለጥ የሚያግዙ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ እንዲመቻች አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፣ ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፣ያረጋግጣል፡፡