የግዢ ሥራ አስፈጻሚ
የግዥ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-
- የግዥ አፈጻጸም ተግባራትን በመምራት፣የሀገር ውስጥና የውጭ የግዥ አፈጻጸም ስርዓትን በመዘርጋትና ተፈጻሚነቱን በማረጋገጥ፤ የግዥ ውል አስተዳደር ስራዎችን በመከታተልና እና በግዥ አፈጻጸም ግብረ መልስ በመቀበልና የመፍትሄ እርምጃ በመውሰድ፤ ግዥ በሚፈለገው ጥራት፣ ጊዜና መጠን እንዲፈጸም በማድረግ የተቋሙን ፍላጎት ያረካል፡፡
- በተቋሙ ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች የግዥ ፍላጎት እንዲሰበሰብ በማድረግ እና ከተፈቀደው በጀት ጋር መጣጣሙን በማረጋገጥ ዓመታዊ የግዥ እቅድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
- የሥራ ክፍሉን በአስፈላጊ ግብአቶች ያደራጃል፣ ምቹ የሥራ ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
- በስራ ክፍሉ ውስጥ ያሉ ሰራተኞችን ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፡፡
- የሠራተኞችን የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ ውጤታማ የሆኑ ሰራተኞችን ያበረታታል፣ የአቅም ክፍተት ያለባቸውን ሰራተኞች በመለየት ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
- የሥራ ክፍሉን የአሠራር ችግሮች በመለየትና በማጥናት ምቹ የአሰራር ሂደት እንዲኖር ያደርጋል፣ ተፈጻሚነቱን ያረጋግጣል፡፡
- ወቅታዊ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡፡
- በስራ ክፍሉ ተመድበው የሚሠሩ ሠራተኞች በሙያው በቂ ክህሎትና የትምህርት ዝግጅት ያላቸው እንዲሆኑ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ጋር በጋራ ይሠራል፡፡
- የግዥ ሂደቶች በቴክኖሎጂ /E-Procurement/ የታገዙ እንዲሆኑ ለማድረግ ለሁሉም የግዥ ክፍል ሠራተኞች በቴክኖሎጅው ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንዲያገኙ ቅድመ ሁኔታዎች ያመቻቻል፡፡
- ከፍተኛ ግዥ ለመፈፀም የሚወጡ የጨረታ ማስታወቂያዎችንና የአሸናፊ ድርጅት መረጃ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ላይ እንዲጫን ያደርጋል፡፡
- ግዥ ለመፈጸም እንዲያስችል የወጡ የመንግስት ግዥ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በአግባቡ ሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል፡፡
- ለግዥ አገልግሎት የሚፈለገውን ተግባር በብቃት ለማከናወን የሚቻልበትን ከአድልኦ ነጻ የሆነ ግልጽና ተጠያቂነት ያለበት የአሠራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተፈጻሚ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
- ከየሥራ ክፍሉ የሚቀርቡ አስቸኳይ ግዥዎች በመንግስት ግዥ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሰረት እንዲገዙ ያደርጋል፡፡
- ለሚፈፀሙ ግዥዎች ተፈላጊው የጥራት ደረጃና መጠን የሚያሳይ ዝርዝር መግለጫ እንዲወጣ ያደርጋል፣ ግዥዉ ሲፈፀምም በወጣው ዝርዝር መግለጫ መሰረት መሆኑን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፡፡
- በቡድን መሪው ተረጋግጦ የቀረበለትን የጨረታ ሰነድ ረቂቅ በመመርመር ለአጽዳቂ ኮሚቴ ያቀርባል፡፡
- አዳዲስ የግዥ ፍላጎቶች ከስራ ክፍሎች ሲቀርቡ በእቅዱ ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ በአጽዳቂ ኮሚቴው በኩል ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ቀርቦ እንዲፀድቅ ያደርጋል፡፡
- በተቋሙ የሚከናወኑ የዕቃ፣ የአገልግሎትና የግንባታ ግዥዎች በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ በተያዘላቸው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት እንዲገዙ በበላይነት ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣
- ስለ ግዥ እንቅስቃሴዎች የሚቀርቡትን የተለያዩ ዘገባዎችንና ስታትስቲካዊ የሪፖርት መግለጫዎች ያረጋግጣል፡፡
- በተቋሙ የሚፈፀሙ ግዥዎች ከአየር ንብረት ብክለት ነፃ የሆኑ መሆናቸዉን ያረጋግጣል፡፡
- የግዥ ሂደቱ በቴክኖሎጅ /E-Procurement/ የታገዘ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
- የቴክኒክና የፋይናንስ ግምገማዎች በወጣው የጨረታ ሠነድ መሰረት የተከናወነ መሆኑን በማረጋገጥ ለአጽዳቂ ኮሚቴ ያቀርባል፡፡
- የቴክኒክና የፋይናንስ ግምገማ ውጤት ለተጫራቾች በተመሳሳይ ጊዜ እንዲገለፅ ያደርጋል፡፡
- የቴክኒካል ግምገማቸዉ ከመስሪያ ቤቱ አቅም በላይ የሚሆኑ የዕቃ፣ አገልግሎትና የግንባታ ግዥዎች አቅም ባላቸው አካላት እንዲገመገም ለመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ ያቀርባል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ፣ ለውል ማስከበሪያና ለቅድመ ክፍያ የሚያስፈልጉ ዋስትናዎች መያዛቸውን ይቆጣጠራል አፈፃፀሙንም ይከታተላል፡፡
- በጨረታ አከፋፈት ስነ ስርዓት ጊዜ በጨረታ አከፋፈቱ ወቅት የሚከናወኑ ሁነቶች በቃለ ጉባዔ እንዲያዙ እንደአስፈላጊነቱም በፎቶና በቪዲዮ እንዲደገፍ ያደርጋል አፈፃፀሙንም ይከታተላል፡፡
- ከአቅራቢዎች ለሚቀርቡ የማብራሪያ ጥያቄዎች በጽሁፍ ማብራሪያ ይሰጣል፤እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡
- ከተቋሙ ውጭ ባሉ የግዥ አገልግሎት ፈጻሚ ድርጅቶች /Outsource/ ተደርገው እንዲገዙ ውሳኔ የተሠጠባቸው የዕቃ፣ አገልግሎትና የግንባታ ግዥዎችን ክትትል ያደርጋል፡፡
- በመንግስት ግዥ ላይ እንዳይሳተፉ የታገዱ አቅራቢዎች መስሪያ ቤቱ በሚያከናውነው ማንኛውም ግዥ ላይ እንዳይሳተፉ ቁጥጥር ያደርጋል፤
- ከውጭ ሀገር ተገዝተው ለሚገቡ ዕቃዎች ዲክላራሲዮንና ኮሜርሽያል ኢንቮይስ ወደ ባንክ በመላክ ሂሳብ እንዲወራረድ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፡፡
- ግዥ አፅዳቂ ኮሚቴው ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ይሠጣል ወይም በሚመለከተው ባለሙያ እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡
- የአገር ውስጥ አምራቾችን፣ ሥራ ተቋራጮችንና አገልግሎት ሠጭ ድርጅቶች የግዥ ህጉ በሚፈቅደው መሠርት ልዩ ተጠቃሚ /Domestic preference/ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
- በለጋሽ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ የሚከናወኑ ግዥዎች በለጋሹ አካል የውል ስምምነት መሠረት እንዲከናወን ያደርጋል አፈፃፀሙንም ይከታተላል፡፡
- በመስሪያ ቤቱ ለሚከናወኑ ግዥዎች አጋዥ እንዲሆን የወቅቱ የገበያ ዋጋ በባለሙያ እንዲጠና ያደርጋል፡፡
- የዕቃ፣ አገልግሎትና የግንባታ ግዥ ሲፈጸም የሚቀርበው ዋጋ የወቅቱ የገበያ ዋጋ ስለመሆኑ በገበያ ጥናት እንዲረጋገጥ ያደርጋል፡፡
- በውል አስተዳዳር ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮች ሲኖሩ ለችግሩ መፍትሄ የሚሆን በጥናት ላይ የተመሠረተ የውሳኔ ሃሳብ ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ያቀርባል፡፡
- የዋጋ ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸው ውሎች ተፈፃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የወቅቱን የገበያ ዋጋ በጥናት እንዲረጋገጥ ያደርጋል፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፡፡
- ከመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ በተሠጠው የገንዘብ ውክልና መጠን ከአቅራቢዎች ጋር ውል ይፈራረማል እንደአስፈላጊነቱም የውል ድርድር ያደርጋል፡፡
- ለዕቃ፣ ለአገልግሎትና ለግንባታ ግዥ የተመረጡ ዝርዝር የፍላጎት መግለጫዎች ግልፅና አሳታፊ መሆኑን በጥናት ያረጋግጣል፡፡
- ለሙስና አጋላጭ የሆኑ የግዥ አካሄዶችን በጥናት በመለየትና የሌሎች ሀገራትን ምርጥ ተሞክሮ በመቀመር ግልፅ የሆነ የግዥ የአሰራር ስርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል ፡፡
- የሚቀርቡ ዕቃዎች፣ አገልግሎቶችና የግንባታ ሥራዎች ቀደም ሲል በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠውና በተገባው የውል ስምምነት መሠረት እንዲቀርቡ ያስተባብራል፤አፈፃፀሙንም ይከታተላል፡፡
- ዓለም አቀፍ ግዥ ሲፈፀም አዋጭ የሆነውን ዓለም አቀፍ የንግድ ውል ስምምነት /ኢንኮተርም/ በጥናት ላይ በተመሠረተ ሁኔታ በመለየት ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤፡፡
- የግዥና የውል አስተዳደር ሰነዶችን በአግባቡ እንዲደራጁ በማድረግ ለውስጥና ለውጭ ኦዲተሮች ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
- ከስራ ባህርያቸው አንጻር በመንግስት ግዥ አዋጅና መመሪያ መሠረት ለመፈጸም የሚያስቸግሩ ግዥዎችን በማጥናትና በመለየት ልዩ የአፈፃፀም መመሪያ ለማዘጋጀት እንዲቻል ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ኃሳብ ያቀርባል፤ሲፈቀድም በባለሙያዎች እንዲዘጋጅ ያደርጋል፡፡
- የግዥ ውል ሂደት በሚገባ መካሄዱን ይቆጣጠራል፣ ኮንትራታቸውን በአግባቡ የማይወጡትን በመመሪያ መሰረት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡
- በፌዴራል የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በኩል የሚፈጸሙ የጋራ መጠቀሚያ ዕቃዎች እንዲሁም የአገልግሎትና የግንባታ ግዥዎች በተገባው ዉል መሰረት መፈፀሙን ይከታተላል፡፡
- ቁልፍ የግዥ አፈፃፀም መለኪያዎችን (KPI) መሠረት በማድረግ የተቋሙን የግዥ አፈፃፀም ክንውን እንዲገመገም ያደርጋል፡፡
- በፌዴራል የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በኩል የሚፈጸሙ የጋራ መጠቀሚያ ዕቃዎች ዝርዝር በማውጣት በወቅቱ ለአገልግሎቱ እንዲላክ ያደርጋል፤አፈፃፀሙንም ይከታተላል፡፡
- ለግንባታ ሥራ ተቋራጮች እንዲሁም ለእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች መድረክ በማዘጋጀት በግዥ ሂደቱ ዙሪያ አስተያየት ይቀበላል፣ የማስተካከያ ርምጃዎችን ይወስዳል፡፡
- ከውስጥም ሆነ ከውጭ ተገልጋዮች የሚቀርቡ የግዥ አቤቱታዎችን፣ ቅሬታዎችን እና ጥቆማዎችን እንዲጣሩ ከመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ትዕዛዝ ሲሰጥ ተቀብሎ እንዲጣራ ያደርጋል፣ ውጤቱንም ያሳውቃል፡፡አቅራቢዎች በውል አተገባበርና በዋጋ ማስተካከያ ዙሪያ ላቀረቧቸው ጥያቄዎች የአፈፃፀም ግብረ መልስ እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡
- ከውጭና ከውስጥ ኦዲተሮች እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በግዥ አፈፃጸሙ ላይ የሚሰጡ አስተያየቶችን ተቀብሎ ግብረ መልስ ይሠጣል፡፡
- የተቋሙን የግዥ አፈፃፀም ሪፖርት በየሩብ ዓመቱ በማዘጋጀት ለፌዴራል የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ መላኩን ያረጋግጣል፣ይከታተላል፡፡