የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ሥራ አስፈጻሚ
የሥነ ምግባር መከታተያ ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለግብርና ሚኒስትር ጽ/ቤት ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-
- የክፍሉን ስራዎች በማቀድና በመምራት፤የስነ ምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል፣ የሙስና ሥጋት ተጋላጭነት ጥናት፣ የኦንላይን የሀብት ማሳወቅያና ምዝገባ ፣ የጥቅም ግጭት መከላከል ስርዓቶች ተግባራዊ በማድረግ፣ የሙሰና መረጃ የማመንጫት ሥርዓት በመዘርጋት፣ የጠቋሚዎች የከላላ ሰርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግና በመከታተል በተቋሙ ሥነምግባር እንዲሰፍን በማድረግ እና ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ይከላከላል፡፡
- የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ ያቅዳል፤ ያስተበባብራል፤ ሥራውን በበላይነት ይመራል፣ ያደራጃል፤ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
- ለሥራው የሚያስፈልገው በጀት፣የሰው ኃይል እና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች እንዲሟሉ በማድረግና የተመደበ ሀብት ለታለመላቸው ዓላማ በአግባቡ እንዲውሉ ክትትል ያደርጋል፤
- ለሥራ ክፍሉ ባለሙያዎች በተመደቡበት የሥራ መዘርዝር መሠረት የሥራ ክንውኖችን ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊውን ማስተካከያ ያደርጋል፤
- ዳይሬክቶሬቱን ውጤታማ ለማድረግ የተቀየሱ አሰራሮች በተገቢው መንገድ ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል፤ተቋሙን በመወከል በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችና ስብሳበዎች ላይ ማብራሪያ እና መረጃዎች ይሰጣል፤
- ከሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሚሰጡ አዳዲስ አቅጣጫዎችን፣ ወቅታዊና ተለዋጭ ሁኔታዎችን እና አሠራሮችን ተቀብሎ ለተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች ግልጽ የማድረግና ከኮሚሽኑ በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት እንዲተገበር ያደርጋል፤
- የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድና አፈፃፀም ሪፖርት ከባለሙያዎች ጋር በየጊዜው ይገመግማል፣ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን ይለያል፣ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል፣ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤
- የአፈፃፀም ሪፖርት ለኮሚሽኑ እና በግልባጭ ለተቋሙ የበላይ ኃላፊ ያቀርባል፣ የፅሑፍ ግብረ መልስ ይቀበላል፣ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
- ለተቋሙ ሰራተኞች እና አመራሮች የስልጠና ፍላጎት እና የስልጠና ርእሶች በዳሰሳ ጥናት እንዲለዩ ያስተባብራል፤
- የተለያዩ የመንግሥት ተቋማትን ተሞክሮዎች በመቀመር የማሰልጠኛ ሰነዶች እና መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤ በተቋሙ ሠራተኞች ያስተቻል፤ ሥራ ላይ እንዲውል ክትትል ያደርጋል፣
- የስልጠና መረጃዎች ተደራጅቶ እንዲያዙ ያደርጋል፤ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያደርጋል፤
- የስልጠና ስትራቴጂና ፕሮግራም እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ በጀት ያስመድባል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- በሥነምግባር ስልጠና የገኘውን የስነ ምግባር ምጣኔ ደረጃ ይለካል፣ ለኮሚሽኑ እና ለተቋሙ ያሣውቃል፤
- በኮሚሽኑ የተዘረጋውን የስልጠና ምዘና፣ የሥነምግባር ተደራሽነት እና የጥራት ማረጋገጫ ስርዓት (Ethics and Integrty Framework) ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፡፡