የኦዲት ሥራ አስፈጻሚ
የኦዲትና እንስፔክሽን ተጠሪነቱ ለግብርና ሚንስትር ጽ/ቤት ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡-
- የስራ ክፍሉን ሥራ በመምራት የተቋሙ ሀብት ህግና ደንብ ተከትሎ ስራ ላይ መዋሉንና የተመደበው ሀብት ጠቀሜታ ማስገኘቱን በኦዲት በማረጋገጥ፣ የኦዲት ግኝቶች ላይ የተሰጠው የኦዲት አስተያየት ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ መወሰዱን በመከታተል፣ ጠንካራ የፋይናንስ አስተዳደር እና የሥራ አፈጻጸም ሥርዓት በተቋሙ እንዲኖር በማድረግ፣ የተቋሙን ሃብት ከብክነት ለመጠበቅ ነው፡፡
- የክፍሉን ሥራ በበላይነት ያስተባብራል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣ ውሳኔ ለሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ውሳኔ ይሰጣል፡፡
- የተቋሙን የሥጋት ተጋላጭነት የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የስጋት አካባቢን በመለየት የክፍሉን ዓመታዊ የፊዚካልና የፋይናንስ ዕቅድ ያዘጋጃል፤ ከሚመራቸው ቡድን መሪዎች/ ከኦዲት ባለሙያዎች ጋር በመወያየት ያዳብራል፤ ዕቅዱን አጠናቅሮ ለመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ በማፀደቅ ለገንዘብ ሚኒስቴር ያቀርባል፡፡
- የክፍሉን ግብ ለማሳካት የሥራ ክፍሉ አስፈላጊ በሆኑ ግብአቶች እንዲሟላ ያደርጋል፡፡
- በክፍሉ የሚከናወኑ ሥራዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ፣ ወጪና ጥራት መሰረት ውጤታማ በሆነ መልኩ መከናወናቸውን ይገመግማል፣ ያረጋግጣል፡፡
- በክፍሉ የሚታዩ የአሰራር ክፍተቶችና ችግሮችን ይለያል፣ የማሻሻያ እርምጃዎች ይወስዳል፡፡
- የጸደቀ የክፍን እቀድ መሠረት አድርገው የኦዲት ዕቅድ እንዲያዘጋጁ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን በየወቅቱ ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ግብረ-መልስ ይሰጣል፡፡
- የዴስክ ሃላፊዎች /ባለሙያዎች የተሟላ ዕውቀትና ክህሎት እንዲኖራቸው እና ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ ዘላቂ የሰው ሃይል ልማት እንዲኖር ያደርጋል፡፡
- በዴስክ ሃላፊዎች ደረጃ ያልተፈቱ ችግሮች እና ከስራ ክፍሎች የሚቀርቡ ቅሬታ ይቀበላል፣ ያወያያል፣ ችግሩ እንዲፈታ ያደርጋል፡፡
- በስራ ክፍሉ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም፣ የመልካም አስተዳደር እና ሌሎች የባለ ብዙ-ዘርፍ (cross-cutting) ጉዳዮች በመደበኛ ስራዎች እንዲካተቱና እንዲተገበሩ ያደርጋል፤ አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል፣ ይመራል፣ ያስተባብራል፡፡
- የክፍሉን ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ ከበላይ አመራር፣ የሥራ ክፍሎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ለመስራት የሚያስችሉ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ይዘረጋል፡፡
- የኦዲት ፕሮግራም እዲዘጋጅ ያደርጋል፡፡
- ከተቋሙ የበላይ ኃላፊ እና ከኦዲት ተደራጊ የሥራ ክፍሎች ጋር የመግቢያ ስብሰባ በማከናወን ስለሚካሄደው ኦዲት አስፈላጊውን ማብራሪያ ይሰጣል፡፡
- በሥራ ላይ ያሉ የፌዴራል መንግሥት አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በስራ ላይ መዋላቸውን በህጋዊነት ኦዲት እንዲረጋገጥ ያደርጋል፡፡
- ተቋሙ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚከተለው የሥራ አፈጻጸም ስልት ኢኮኖሚያዊ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ መሆኑን ለማረጋገጥ የክዋኔ ኦዲት እዲከናወን ያደርጋል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፡፡